ዜና፡ በአማራ ክልል በከባድ መሣሪያ ጭምር ታግዞ እየተካሄደ ባለው የተኩስ ልውውጥ በሲቪል ሰዎች ላይ የሞት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ደርሷል- ኢሰመኮ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26/2015 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች በመከላከያ ሰራዊትና ታጣቂዎች መካከል በከባድ መሣሪያ ጭምር ታግዞ እየተካሄደ ባለው የተኩስ ልውውጥ በሲቪል ሰዎች ላይ የሞት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ይህን የገለፀው በአማራ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው “የሕግ ማስከበር