ዜና፡ የሀገራዊ የፍትህ ስርአቱ በትግራይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ለመዳኘት የተሟላ ቁመና ይኖረዋል ብለን አናምንም ሲሉ የትግራይ ግዝያዊ ኣስተዳደር ፕሬዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15/ 2015 ዓ.ም፡- የሀገራዊ የፍትህ ስርአቱ በትግራይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ለመዳኘት የተሟላ ቁመና ይኖረዋል ብለን አናምንም ሲሉ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ። የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንቱ ለክልሉ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት መግለጫ ፍትህ መረጋገጥ እንዳለበት ጠቅሰው የፖለቲካ መፍትሄዎች እና ሰላም በተሟላ መልኩ