ዜና፡ በመዲናዋ የጎዳና ላይ ሕፃናት በመንግስተ የፀጥታ ሃይሎች “በኃይል፣ በዘፈቀደና በሕገ-ወጥ አሠራር” በጅምላ እንደሚታፈሱ ኢሰመኮ አስታወቀ
ፎቶ- ዘጋርዲያን አዲስ አበባ፣ 28/ 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የጸጥታ አካላት ከከተማዋ በጎዳና ላይ የሚገኙ ሕፃናትን በኃይል፣ በዘፈቀደና ሕጋዊ ባልሆነ አሠራር በአፈሳ መልክ በማንሳት የተሟላ አገልግሎት በሌለበት አቃቂ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የተሃድሶ ማዕከል እንዲቀመጡ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኢሰመኮ በአዲስ አበባ ከተማ የጎዳና