ዜና ትንታኔ፡ የሱዳን ሀይሎች ድርድርን አዲስ አበባ ታስተናግዳለች ተባለ፤ የሱዳን መንግስት የኬንያ ፕሬዝዳንትን ዋና አደራዳሪነትን እንደማይቀበለው ገለጸ
በሚሊዮን በየነ @MillionBeyene አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9/2015 ዓ.ም፡- በሱዳን ተቀናቃኝ ሀይሎች መካከል የተነሳው ግጭት ከተጀመረ ሁለት ወራትን ደፍኗል። ግጭቱ ሁለት ሚሊየን ሱዳናውያን እንዲፈናቀሉ ከማድረጉ በላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሂወታቸውን አጥተዋል። በጀነራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን የሚመራው የአገሪቱ መከላከያ ሀይል እና በጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ የሚመራው የፈጥኖ ደራሽ ልዩ