ዜና፡ ባሕርዳር፣ ጎንደርና ላሊበላን ጨምሮ በስድስት ከተሞች የሕዝብ የአገልግሎት ሰጪ፣ የመንግሥት፣ የማኅበረሰብና የንግድ ተቋማት ከነገ ጀምሮ አገልግሎት እንዲሰጡ ታዘዘ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3/ 2015 ዓ.ም፡- የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ በባሕርዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ሸዋ ሮቢትና ላሊበላ የሕዝብ የአገልግሎት ሰጪ፣ የመንግሥት፣ የማኅበረሰብና የንግድ ተቋማት ከነገ ነሐሴ 4/2015 ጀምሮ ክፍት እንዲሆኑ አዘዘ። የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ የተለያዩ ትዕዛዝችና ክልከላዎችን ደንግጓል፡፡ ጠቅላይ