ጤና/ ትንታኔ፡ የጥርስ ጤንነት፡ “ህብረተሰቡ የሚጠቀማቸው ከርካታ ከተክሎች የሚገኙ የእንጨት መፋቂያ አይነቶች ጸረ ባክቴሪያ እና ጸረ ፈንገስ የተፈጥሮ ንጥረ ነገር ያላቸው ናቸው ”- ጥርስ ህክምና ባለሙያ ዶ/ር ሽመልስ ተኮላ
photo credit: ERIC LAFFORGUE በሚሊዮን በየነ @MillionBeyene አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8/2015 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ እ.አ.አ ከ2010 እስከ 2020 በተደረገ ጥናት የጥርስ ጤንነት አጠባበቅ ልማድ እጅግ አነስተኛ መሆኑ ተረጋግጧል። በኢትዮጵያ የጥርስ ጤንነት አጠባበቅ ልማድ ያላቸው ሰዎች አስራ ሁለት ነጥብ ሁለት በመቶ የሆኑ ዜጎቿ ብቻ ናቸው ሲል ኔቸር የተሰኘ