ጥልቅ-ትንታኔ፡ የኢትዮጵያ መንግስት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት መርማሪ ቡድን እሰጣገባ፤ ፍራቻ የተላበሰ የፖለቲካ ውሳኔ ወይስ ሉአላዊነት ?
በሚሊዮን በየነ @MillionBeyene አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15/ 2015 ዓ.ም፡- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ያቋቋመው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ ኮሚሽን በምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ሪፖርት አቅርቧል። በቀረበው ሪፖርት ላይ ተመርኩዘው አባል ሀገራቱ የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። ምክር ቤቱ መርማሪ ኮሚሽኑን ካቋቋመበት ግዜ ጀምሮ