ዜና፡ ጎጎት ፓርቲ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት እና በሁለት ባለስልጣናት ላይ ከጉራጌ እራስን በእራስ ማስተዳደር መብት ጋር በተያያዘ ክስ መሰረተ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6/2015 ዓ.ም፡- ጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ መንግስት ያቀረበውን የክላስተር አደረጃጀት በመቃወም በአምስት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ እና በሁለት ባለስልጣናት ላይ ክስ መመስረቱን አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የጉራጌ ህዝብ በራሱ ክልል እንዲደራጅ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን ተከትሎ ይህንኑ ህገ መንስታዊ መብቱን ለማስፈፈጸም በህጉ መሰረት ለደቡብ ክልል ምክር ቤት እና ለፌደሬሽን ምክር ቤት ህዝበ ውሳኔ እንዲያደራጁለት አቤቱታዎችን ያቀረበ ቢሆንም ምንም ምላሽ ባለመሰጠቱ ወደ ክስ ማምራቱን ፓርቲው ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ አመላክቷል።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ህዳር 17 ቀን 2011 ዓ.ም የጉራጌ ህዝብ በራሱ ክልል እንዲደራጅ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን ያወሳው የፓርቲው መግለጫ በተመሳሰይ ከአንድ አመት በፊት ነሃሴ 5 ቀን 2014 ዓ.ም የጉራጌ ዞን ም/ቤት የብልጽግና መንግስት ያቀረበውን የክላስተር አደረጃጀት ምክረ ሀሳብ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ ማድረጉን ጠቁሟል።

በፓርቲው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የመሰረታዊ መብቶች እና ነጻነት ችሎት ክስ የተመሰረተባቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ባለስልጣናትም

1. የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልል መንግስት ምክር ቤት

2. የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞከራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌደሬሽን ምክር ቤት

3. የብልጽግና ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤት

4. አቶ አገኘሁ ተሻገር

5. የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

6. አቶ አለማየሁ ባውዴ

7. የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን መሆናቸውን በጋዜጣዊ መግለጫው አስታውቋል።

ክሱ የመሰረተው ፓርቲው በወከላቸው ከ25 በላይ በሆኑ ጠበቆች አማካኝነት መሆኑን ገልጿል። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተመላከተው የክሶቹ ዋነኛ ጭብጥም አንደኛ ተከሳሽ የደቡብ ክልል ምክር ቤት የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ወስኖ ባቀረበለት መሰረት በአንድ ዓመት ለጉራጌ ህዝብ ህዝበ ውሳኔ ባለማደራጀቱ፣ ሁለተኛ ተከሳሽ የፌደሬሽን ም/ቤት የደቡብ ክልል ም/ቤት ህገ መንግስታዊ ህዝበ ውሳኔ የማደራጀት ሀላፊነቱን ባለመወጣቱ የሚሉት ይገኙበታል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.