ዜና፡ ሁለቱን የሱዳን ተቀናቃኝ ጀነራሎች ፊት ለፊት አገናኝተው ለማወያየት የኬንያው ፕሬዝዳን ቃል ገቡ፤ ዶ/ረ ወርቅነህ ገበየሁ በድጋሚ ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6/2015 ዓ.ም፡- ኢጋድ አገራት መሪዎች ትናንት ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ጅቡቲ ላይ ባካሄዱት ጉባኤ ዶ/ረ ወርቅነህ ገበየሁ ለተጨማሪ አራት አመታት በጸሓፊነት እንዲመሩ በድጋሚ መምረጡ ተገለጸ። ጅቡቲ የወቅቱን የሊቀመንበርነት ቦታ ከሱዳን ተቀብላለች። ጉባኤው በእኔ ላይ ሙሉ እምነት አሳድሮ ለተጨማሪ አራት አመት በጸሐፊነት እንድመራ እድሉን ስለሰጠኝ አመስግናለሁ ሲሉ ዶ/ር ወርቅነህ በማህበራዊ ሚዲያ ትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜና በጂቡቲ በተካሄደው የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ የሱዳንን ግጭት ለማሸማገል አራት ሀገራት ያሉት አሸማጋይ ቡድን ይፋ ተደርጓል። ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን በአሸማጋይነት የተመረጡ የኢጋድ አባል ሀገራት ሲሆኑ ቡድኑን የምትመራው ኬንያ መሆኗም ተጠቁሟል።

የኬንያው ፕሬዳንት ሩቶ ሁለቱን የሱዳን ተቀናቃኝ ሀይሎች ፊት ለፊት አገናኝተው ለማሸማገል ቃል መግባታቸውን የፈረንሳይ የዜና ወኪል ኤኤፍፒ በዘገባው አስታውቋል።  ሁለቱንም ጀነራሎች ከኢጋድ አባል ሀገራት መካከል በአንዱ ዋና ከተማ ተገናኝተው እንዲወያዩ ለማስቻል እንደሚሰራ የኬንያው ፕሬዝዳን ሩቶ ጽህፈት ቤት ይፋ ባደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ ማስታወቁን ዘገባው አመላክቷል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.