ዜና፡ ኦፌኮ ያገረሸው ጦርነት እንዲቆም ጠየቀ፣ አለም አቀፍ ሸምጋዮች የሰብአዊ እርቅ ጊዜውን ተጠቅመው ሰላም ለማምጣት ባለመቻላቸውና በኦሮሚያ ያለውን ግጭት ትኩረት ባለመስጠታቸው መጸጸቱን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25/2014፡- የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እና በኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ግጭትን በማቆም ሰላማዊ መፍትሄ እንዲሹ ጠየቀ፡፡ ኦፌኮ ክልላዊ እና አለም አቀፋዊ ሸምጋዮች የሰብአዊ እርቅ ጊዜውን ተጠቅመው ተፋላሚ ወገኖችን ወደ ድርድር ጠረጴዛ ማምጣት እና አጠቃላይ የተኩስ አቁም ስምምነት ማሰፈን