የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የቀድሞዋን የአለም አቀፍ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሊቀመንበር አድርገው ሾሙ

ፋቱ ቤንሱዳ

የሰብአዊ መብቶች ካውንስል ፕሬዝዳንት አምባሳደር ፌዴሪኮ ቪሌጋስ (አርጀንቲና) ጋምቢያዊቷ ፋቱ ቤንሱዳ፣ ኬንያዊቷ ካሪ ቤቲ ሙሩንጊ እና አሜሪካዊቷን ስቲቨን ራትነር በኢትዮጵያ የአለም አቀፍ ሰበአዊ መብቶች ኮሚሽን  ሶስት አባላት ሆነው መሾማቸውን አስታውቀዋል።  ወይዘሮ ቤንሱዳ የሶስቱ  ኮሚሽኖች ሊቀመንበር ሆነው አንሚያገለግሉ ታውቋል።

በታህሳስ 17 ቀን 2021 በ S-33/1  ስብሰባ  ባወጣው የውሳኔ ሰበአዊ መበት ካውንስል የአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ኮምሽን በሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እንዲሾም ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን ገለልተኛ ምርመራ ለማካሄድም ወስኗል ። ከህዳር 3 ቀን 2020 ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ በተፈጠሩት ግጭት፣ የሰበአዊ መብት እና የስደተኛ ህግ ጥሰቶችን በገለልተኛ አካል ይመረምራል።

ሶስቱ የተሾሙት ኮሚሽኖች  የተፈጸሙትን የመብት ጥሰቶች እና የመብት ጥሰቶችን በተመለከተ እውነታውን እና ሁኔታዎችን በማጣራት ማስረጃዎችን በማሰባሰብ እና በማቆየት ተጠያቂ የሆኑትን ለመለየት እና በተቻለ መጠን ለቀጣይ እና ለወደፊት ተጠያቂነትን ለመደገፍ መረጃው ተደራሽ እና ጥቅም ላይ እንዲውል እንያዲያደርጉ ተጠይቋል.

በዚሁ የውሳኔ ሃሳብ 47 አባላት ያሉት ኮሚሽኑ የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንን ሪፖርት በማጠናከር እና ተጠያቂነትን በመደገፍ ለኢትዮጵያ መንግስት በቴክኒክ ድጋፍ ላይ ምክረ ሃሳቦችን እንዲያቀርብ አዟል። ኮሚሽነሮቹ በግል ተግባራቸው የሚያገለግሉ ሲሆን በ50ኛው ሰኔ/ሀምሌ 2022 ለሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት የቃል ገለፃ እና በመስከረም/ጥቅምት ወር በሚካሄደው 51ኛ ጉባኤ ላይ የጽሁፍ ሪፖርት እንዲያቀርቡም ተጠይቀዋል።

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.