ዜና፡ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ በኢትዮጵያ የሚያካሂደውን የእርዳታ አቅርቦት ማቋረጡን አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1/2015 ዓ.ም፡- በኢትዮጵ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተጎጂዎች ተብሎ የሚቀርብ እርዳታ ላልታለመለት አላማ እየዋለ መሆኑ በመረጋገጡ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ በኢትዮጵያ የሚያካሂደውን የእርዳታ አቅርቦት ማቋረጡን ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው የኢሜይል መልዕክት አስታወቀ። የምግብ እርዳታ የማቋረጡ ውሳኔ እጅግ አዳጋች እና አስቸጋሪ ቢሆንም ውሳኔውን ለማሳለፍ ተገደናል