ዜና፡ አንድ እስራኤላዊ በጎንደር መታገቱን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5/2015 ዓ.ም፡- በዜግነት እስራኤላዊ የሆነ አንድ ግለሰብ በሰሜን ኢትዮጵያ በአማራ ክልል በጎንደር ታግቶብኛል ሲል የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቀ። እስራኤላዊው የታገተው ማስለቀቂያ ገንዘብ በፈለጉ ሀይሎች መሆኑም ተጠቁሟል። ታጋቹን እስራኤላዊ ለማስለቀቅ ዲፕሎማቶች ከአከባቢው የጸጥታ ሀይሎች እና ከኢንተርፖል ጋር በመቀናጀት እየሰሩ እንደሚገኙ መስሪያ ቤቱ ገልጿል።