ዜና፡ የሀዲያ ዞን ባዴዋቾ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ባካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ሶስት ሰዎች ላይ ጉዳት መደረሱ ተገለፀ
በአብዲ ቢያንሳ @ABiyenssa አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12/ 2015 ዓ.ም፡- የሀዲያ ዞን ምስራቅ ባዴዋቾ ወረዳ ሾኔ ከተማ የመንግስት ሰራተኞች የወር ደመወዝ በጊዜ ስላልተከፈላቸው ባካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ፣ ሰልፉን ለመበተን ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ሶስት ሰዎች ላይ ጥቃት ደርሶ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የወረዳው ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፁ፡፡ ስማቸው እንዲገለፀ ያልፈለጉ በሰልፉ