ዜና፡ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ በበጎ ጎኑ እንደሚያየው አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19/2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ኢትዮጵያን አስመልክቶ ያሳለፈውን ውሳኔ የተመለከተ መግለጫ አውጥቷል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመግለጫው የምክር ቤቱ ውሳኔን በበጎ አይኑ እንደሚያየውም አስታውቋል። መግለጫው አያይዞም ምክር ቤቱ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ትግበራ ላይ የተገኙ ውጤቶችን እውቅና መስጠቱን ገልጿል።