ዜና፡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ግጭት ቀስቃሽ መልእክቶችን የሚያስተላልፉ የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃንን አስጠነቀቀ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15/ 2015 ዓ.ም፡- ለሚከተሉት ሃይማኖት አገልግሎት እንዲጠቀሙበት የተፈቀደውን መገናኛ ብዙኃን በመጠቀም የዜጎችን ሰላምና አብሮነት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ኃላፊነት የጎደላቸው መልእክቶችን በሚያስተላልፉ የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኋን ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ባለስልጣኑ ትላንት ባወጣው መግለጫው እንዳስታወቀው የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ማኛውንም