ዜና፡- የጋምቤላ ክልል “ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመቆጣጠር” የሰዓት እላፊ አዋጁን አጠናከረ

አቶ ኡጌቱ አዲንግ ። ምስል፡ የጋምቤላ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 8፣ 2014 ዓ.ም ፦የጋምቤላ ክልል “በጋምቤላ ከተማ ባለው ነባራዊ ሁኔታ” እና “ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመቆጣጠር” በሚል ቀደም ሲል በክልሉ ተጥሎ የነበረውን የሰዓት እላፊ አዋጅ እያጠናከረ መሆኑን ትናንትና  ሀሙስ ሐምሌ 8  ቀን 2014 ዓ.ም. አስታወቀ።

የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡጌቱ አዲንግ እንደገለፁት በቅርቡ በጋምቤላ ከተማ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት በክልሉ ፕሬዝዳንት አማካኝነት የሰዓት እላፊ እገዳ ተጥሎ እንደነበር አስታውሰው  “የህብረተሰቡን ደኅንነት” ለማረጋገጥ በወጣው የሰዓት እላፊ አፈጻጸም ላይ ክፍተት አለው ብለዋል።

ይህ ወሳኔ  ጋምቤላ ከተማ ልክ  የዛሬ ወር ሰኔ 7 ቀን የፌደራል መንግስትና የክልሉ ሃይሎች ከጋምቤላ ነጻ አውጪ ጦር  እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት  የጣምራ አማፂ ሃይሎች ጋር አንድ ሙሉ ቀን በፈጀ ከፍተኛ ውጊያ ካደረጉ በኋላ የተላለፈ ነው። በወቅቱ በነበረው ጦርነት ከተማዋ መናወጧ ይታወሳል። 

የክልሉ መንግስት በዚያን ጊዜም የሰአት እላፊ እገዳ የጣለው  “ከከባድ ጦርነት” በኋላ “ከተማዋ ከፊል ነፃ ወጣች” ብሎ ካወጀ  በኋላ ሲሆን ጦርነቱም “በሁለቱም ወገኖች ላይ ጉዳት አድርሷል” መባሉም ይታወቃል። ነገር ግን ይህ የሰዓት እላፊ እግድ ከተላለፈ  በኋላ በተወሰደ ከባድ እርምጃ የጸጥታ ሃይሎች ሰላማዊ ሰዎችን ሲገድሉ እና ቤት ለቤት እየፈተሹ ከአማፂ ቡድኖቹ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ሰላማዊ ዜጎችን ሲያስሩ ታይቷል።

ትናንት  የወጣው መግለጫ ክልሉ ከዚህ ቀደም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11፡30 ላይ ተጥሎ የነበረውን የሰዎችና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ የሚገድብ ሰዓት እላፊ በተጠናከረ መንገድ  እንዲተገበር የሚያስችልም ነውም ተብሏል።

በዚህም መሰረት ከአምቡላንስ እና የጸጥታ ሃይሎች ተሸከርካሪዎች በስተቀር የሰዎችና ሌሎች ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ የሚፈቀደው ከንጋቱ 11፡30 እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ብቻ መሆኑ ተጠቅሷል። አቶ ኡጌቱ አክለውም በአሁኑ ወቅት በጋምቤላ ከተማ “ሰላማዊ ሁኔታ” እንዳለ ገልጸው በየደረጃው የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎችም የተጠናከረ የመከላከል ስራ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። የጋምቤላ ከተማን ደህንነት ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ በተደራጀ መልክ  መረጃ ለጸጥታ ሃይሎች እንዲያደርሱ ጠይቀዋል። 

በጋምቤላ ክልል የወጣው የሰዓት እላፊ እገዳ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው አሶሳ ከተማ “ጊዜያዊ የሰዓት እላፊ” ከተጣለ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መሆኑ ነው ። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.