ዜና፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አዲስ ለተቋቋመው የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ ጊዜያዊ ፍቃድ ሰጠ

አዲስ አበባ ሃምሌ 10፣ 2014 ዓ.ም፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ህዝብን በዋና ምርጫ ክልልነት ለሚወክለው አዲስ ለተቋቋመው የፖለቲካ ድርጅት የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) ጊዜያዊ የምዝገባ ማረጋገጫ ሰነድ ሰጠ።

ፓርቲው ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው መግለጫ፣ “የሲዳማ ህዝብ ከ135 ዓመታት በፊት ጀምሮ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር፣ ባህልና ቋንቋው እንዲከበር ጠንክሮ ሲታገል የኖረ ታጋይ ህዝብ ነው” ያለ ሲሆን  ራሱን የማስተዳደር እውን ያደረገው ደግሞ “በህዝብ መራራ ትግል” መሆኑን ተልፆ በትግሉም  ክልላዊ መንግስት መሆን ችሏል ብሏል። ፓርቲው አክሎም ይህ “ራስን በራስ የማስተዳደር ሕገ መንግሥታዊ መብት በአግባቡ አልተመለሰም። በተግባር አሁን ባለው አገራዊ ሥርዓት ክልሎች የሚተዳደሩት በማዕከላዊ መንግሥት በተሾመ ሥልጣን ነው። ይህም በህገ መንግስቱ የተደነገገው የክልሎች ባለቤትነት/ሉዓላዊነት እየተሸረሸረ በመምጣቱ ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው ገዥ ፓርቲ ማዕከላዊነት በመያዙ ነው” ሲል መግለጫው ገልጿል።

በህዳር 2011 ዓ.ም በተካሄደው ህዝበ ውሳኔ ከ2.3 ሚሊዮን በላይ መራጮች በአብላጫ ድምጽ የሰጡበት የሲዳማ ክልል የኢትዮጵያ 10ኛ ክልላዊ መንግስት መሆኑ ይታወሳል ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክልሉ በገዢው ብልፅግና ፓርቲ እየተተዳደረ ይገኛል።

በተጨማሪም የሲዳማ ክልል የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ የባህልና የፍትህ ሴክተሮች “ትክክለኛውን መንገድ አልተከተሉም” እየተባለ  ሲሆን  ክልሉ ምክንያታዊነት የጎደለው “የስራ አጥነት ቀውስ፣ የፍትህ እጦት፣ ሙስና፣ ጎሰኝነት፣ አድሎና አድሎአዊ ድርጊቶች እየተስተዋለ ነው” ሲል ፓርቲው  ተችቷል፣ አክሎም ይህ  “የማግለል ፖለቲካ ስርዓት” ነውም ብሎታል .

የሲዳማ ህዝብ ትግል መሰረታዊ ዓላማን እውን ለማድረግና ህዝቡ እየደረሰበት ያለውን ችግር ለመቅረፍ ህዝቡን አደራጅቶ የሚታገል ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲ ባለመኖሩ  ህዝቡ ለከፋ ችግር እንዳይጋለጥ ጥቅሙን የሚያስከብረለት ተገዳዳሪ ያስፈልጋል ሲል በመግለጫው አብራርቷል።

ሲፌፓ የተቋቋመው እነዚህን “የህዝባችን መሰረታዊ ጥያቄዎችን” ለመመለስ መሆኑን ገልጿል። አክሎም ምስረታውም አሁን ባለው እውነታ በሚፈለገው ደረጃ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ለማካተት የተደራጀ የፖለቲካ ፓርቲ አስፈላጊ ሆኗል ብሏል። በተጨማሪም “በዴሞክራሲያዊ እሴቶች፣ ዴሞክራሲያዊና ህዝባዊ የስልጣን ባለቤትነትን ተግባራዊ ለማድረግ ለመታገል፣ በብዝሃነት እና በውይይት በማመን፣ እውነተኛ ሀገራዊ ፌደራሊዝምን በመከተል እውን ለማድረግ ተመሳሳይ ግብ ካላቸው ብሄራዊ ፓርቲዎች ጋር ይሰራል” ሲል የፓርቲውን አስፈላጊነት ገልጿል።

ፓርቲው የቋሚ ምዝገባ ሰርተፍኬት ለማግኘት የሚያስፈልገውን ስራ እያጠናቀቀ ያለ “ጊዜያዊ ኮሚቴ” ማቋቋሙን ገልጿል። ኮሚቴው በአሁኑ ወቅት ዋና መሥሪያ ቤቱን በሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው ሀዋሳ ከተማ በማድረግ ተጨማሪ አባላትን እየመዘገበ መሆኑን በመግለጫው አስታውቋል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.