ዜና፡ የተባበሩት አረብ ኤሚሬት ፕሬዝዳንት ሸክ መሃመድ ቢን ዛይድ ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12/ 2015 ዓ.ም፡- የተባበሩት አረብ ኤሚሬት ፕሬዝዳንት እና የአቡዲያቢ ገዢ ሸክ መሃመድ ቢን ዛይድ ለይፋዊ ጉብኝት ዛሬ ጠዋት ነሃሴ 12/ 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቡ።

አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስለጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ውድ ወንድሜ እና ጓደኛዬ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጣህ።እያደገ የመጣው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት  በመከባበር እና ለጋራ እድገት የጋራ ራዕይ ላይ የተመሰረተ ነው። ዘላቂ ልማትን ለማስቀጠል ትብብራችንን እንቀጥላለን” ሲሉ መልዕክታቸውን ስተላልፈዋል፡፡

ሼክ ቢን ዛይደ በኢትዮጵያ ለመጨረሻ ግዜ ጉብኝት ያደረጉት በ2011 ዓ.ም ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብየ አህመድ ወደ ስልጣን በመጡ ከወራት በኋላ እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ ሸክ ቢን ዛይድ የዩናይትድ አረብ ኤሚሬት ልዑል አልጋወራሽ በነበሩበት ወቅት ሲሆን በጉብኝታቸው ወቅትም የሶስት ቢሊየን ዶላር እርዳታ እና ብድር መስጠታቸው ይታወቃል።

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ሸክ ቢን ዛይድ የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው ይነገራል።

ለጉዳዩ ቅርበት ያለው የአዲስ ስታንዳርድ የዲፕሎማቲክ ምንጮች እደገለፁት ምናልባትም ለኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግን ጨምሮ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና ኢትዮጵያ በርካታ ስምምነቶችን ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በዚህ አመት ጥር ወር ላይ በአረብ ኤምሬትስ ባደረጉት ጉብኝት ሁለቱ ሀገራት በኢትዮጵያ እስከ 2000 ሜጋ ዋት ሊደርስ የሚችል 500 ሜጋ ዋት ኃይል ያላቸውን የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ለማልማት ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።

ከዛ ቀደም ብሎ ከአንድ አመት በፊት ጥር ወር ላይ ጠ/ሚ አብይ አህመድ እና የውጭ ጉዳይና የመከላከያ ሚኒስትሮችን ጨምሮ ልዑካን ቡድናቸው በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ጎብኝት ባደረጉበት ወቅት በሸክ መሃመድ ቢን ዛይድ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.