ዜና ትንታኔ፡ “የዛፍ አንበጣ የእንስሳ መኖ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ሳይቀር አውድሞ ባዶ ነው አስቀረን፤ ከፌደራልም ይሁን ከለጋሾች የተደረገልን ምንም አይነት ድጋፍ የለም”- የትግራይ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ
በሚሊዮን በየነ @MillionBeyene አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ በዘንድሮ የክረምት ወቅትየዛፍ አንበጣ ስጋት ሊኖር እንደሚችል በምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ መከላከያ ድርጅት የኢትዮጵያ ቁጥጥር ቅርንጫፍ ለአዲስ ስታንዳርድ አስታወቀ፡፡ በምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ መከላከያ ድርጅት የኢትዮጵያ ቁጥጥር ቅርንጫፍ ቢሮ ሃላፊ ሒወት ለማ በተለይ ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት በኢትዮጵያየዛፍ አንበጣ