ርዕሰ አንቀፅ፡ የምግብ እርዳታ ስርቆትን ለማውገዝ፣ እርዳታን ማቋረጥ ተጎጂዎችን ሁለት ጊዜ መቅጣት ነው፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሞት ተጋርጦባቸዋል፣ ሊታደጉ ይገባል!
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24/2015 ዓ.ም፡- ብልጽግና መራሹ የለውጥ ሀይል ኢትዮጵያን ተረክቦ ማስተዳደር ከጀመረበት መጋቢት 2010 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ በርካታ አሰቃቂ ሰብአዊ ቀውሶች ተፈጥረዋል። ጦርነት ጨምሮ በርካታ ወታደራዊ ጥቃቶች በኢትዮጵያውያን ላይ ካደረሱት ጉዳት በተጨማሪ የሀገሪቱ በሮች ለውጭ ሀይሎች ክፍት እንዲሆኑ በማድረጉ ቅጥረኞች የበርካታ ኢትዮጵያውያን ህይወት ላይ