ዜና: የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ታስረው የነበሩ ሠራተኞቹ መፈታታቸውን አስታወቀ ፣ ቢሮዎቹ አሁንም እንደታሸጉ ናቸው

በእቴነሽ አበራ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3 ፣ 2014- የኢትዮጵያ ምርት ገበያ  ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ነፃነት ተስፋዬ  ያለምንም ክስ በቁጥጥር ስር ውለው ነበሩ የተቋሙ ስድስቱ ቅርንጫፎች ሰራተኞች ባለፈው ቅዳሜ ከእስር መፈታታቸውን ነገር ግን ቅርንጫፎቹ አሁንም እንደተዘጉ ሲሆን ለመክፈት ውይይት እየተደረገ መሆኑን አቶ ነፃነት አክለው ተናግረዋል።

በጊምቢ ከተማ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ለማ በፍቃዱ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት ከላይ የተገለጹት ሰራተኞች (እሳቸውን ጨምሮ) ለህግ ሳይቀርቡ በዋስ ወጥተዋል። “ምንም ምርመራ ሳይደረግ ለዘጠኝ ቀናት ታስረን ቆየን። ፍርድ ቤትም አልቀረብንም። መታሰራችንም ሆነ መፈታታችን ከበላይ አካላት የመጣ ትእዛዝ መሆኑን ብቻ ነው የነገሩን “ብለዋል፡፡

አቶ ለማ አክለውም ይህ ዜና እስከወጣበት ድረስ ቢሮአቸው አለመከፈቱን ገልፀዋል። አዲስ ስታንዳርድ የአዳማ እና የጊምቢ ከተማ ፖሊስ አስተዳደርን ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

በኦሮሚያ ክልል የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ቅርንጫፎች፤ መቱ፣ ጊምቢ፣ ጅማ፣ በደሌ፣ ነቀምት እና አዳማ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ 1/5ኛ የሚሆኑት ሰራተኞች ይሰሩ የነበረው ቅርንጫፎች ተዘግተው ሰራተኞቻቸው በሚያዝያ ወር መጨረሻ ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ መታሰራቸው ይታወሳል። አስ 

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.