ዜና:- በጋምቤላ ክልል ደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢ የተከሰተ ግጭት አንድ ሰው ሲገደል፣ ከዘጠኝ ሺህ በላይ ሰላማዊ ዜጎች ተፈናቅለዋል

ጌታሁን ጸጋዬ

 አዲስ አበባ መጋቢት 05/2014 – በደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢ በተቀሰቀሰ ግጭት ከ9 ሺህ በላይ የላሬ እና የጂካኦ ወረዳ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። የክልሉ የፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኡጉቱ አዲንግ እንደተናገሩት በቅርቡ በሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጪ ጦር-ተቃዋሚዎች (SPLM-IO) ወታደሮች እና በደቡብ ሱዳን መንግስት መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር በማቋረጥ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል ። በኑዌር ዞን ላሬ እና ጂካኦ ወረዳዎች የሚገኙ የአራት ቀበሌዎች ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ተነግሯል ። 

በደቡብ ሱዳን ድንበር አቋርጠው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት ቀያቸውን ጥለው ከተሰደዱት 9,500 ተፈናቃዮች መካከል አብዛኞቹ ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸው ታውቋል ። የሱዳን ታጣቂዎች የኢትዮጵያን እና የክልሉን ባንዲራዎችን ጨምሮ ሌሎች እቃዎችን መውሰዳቸውንም የክልሉ የፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት በመግለጫው አስታውቋል።

ኡጉቱ የተዘረፉትን እቃዎች ለማስመለስ የጸጥታ ሃይሎች መሰማራታቸውን እና የSPLM-IO ወታደሮች ድንበር አልፈው እንዳይገቡም ተገቢው ጥበቃ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። በግጭቱ ምክንያት ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ደቡብ ሱዳናዎያን  በላሬ እና ጂካኦ ወረዳዎች መኖራቸውን የገለፁ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት ለተፈናቃዮቹ አስቸኳይ እርዳታ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በኑዌር ዞን የላሬ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ኡቦንግ ኡኩን በበኩላቸው በደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢ በተፈጠረው ግጭት የላሬ ወረዳ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል ብለዋል። ተፈናቃዮቹ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውሶች መጋለጣቸውን ጠቁመው የሚመለከተው መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ለጋሽ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። በላሬ ወረዳ የብሊምኩን ቀበሌ ነዋሪዎች መንግስት ለጉዳዩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

ባሳለፍነው ጥር ወር አጋማሽ ላይ በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን በመጡ ታጣቂዎች ጥቃት መፈፀሙ ይታወሳል።  በጥቃቱ ስምንት ሰዎች ሲሞቱ አምስት ሰዎች ቆስለዋል። እንደ ክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አቡላ ኡቦንግ ከሆነ ታጣቂዎቹ ከደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ የመጡ ሲሆን ጥቃቱ የተፈፀመው በኑዌር ዞን አኮቦ ወረዳ ባካንካን ቀበሌ መሆኑን ሲል የክልሉ ፓሊስ በወቅቱ አስታውቋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነሩ ታጣቂ ቡድኖች ወደ ክልሉ የመግባት እና የመውጣት አዝማሚያ እንዳለ ጠቁመዋል። “ወቅቱ በጋ ሲሆን ክልሉን ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያጋራው ድንበር ሰፊ እና ክፍት ነው” ሲሉ ተናግረዋል ። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.