ዜና: የአሶሽየትድ ፕረስ ጋዜጠኞች ላይ 11 የምርመራ ቀን ለሶስተኛ ግዜ ተፈቀደባቸው

ጋዜጠኛ አሚር አማን እና የካሜራ ባለሙያው ቶማስ እንግዳ

ማህሌት ፋሲል  @MahletFasil

አዲስ አበባ መጋቢት 9 2014 – የአራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የግዜ ቀጠሮ ችሎት ዛሬ ቀረቡት የ የአሶሽየትድ ፕረስ ጋዜጠኛ አሚር አማን እና የካሜራ ባለሙያው ቶማስ እንግዳ ላይ ፖሊስ ምርመራን ስላልጨረስኩ 14ተጨማሪ ቀን ይሰጠኝ ሲል ችሎት ጠይቋል ፍርድ ቤቱም 11 የምርመራ ቀናት ለፖሊስ ፈቅዷል::

በዛሬው ችሎት ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም 14 ቀን ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ሲሆን እንደ ምክንያት ያቀረበው “ከተጠርታሪዎች እጅ የተያዙ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ለብሄራዊ መረጃ ና ደህንነት ምርመራ እንዲደርግ ልከናል ፣እንዲሁም መስሪያ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹን በተመለከተ ቴክኒክ ማስረጃ እንዲልኩ ጠይቀን መልስ በመጠባበቅ ላ ነን ያለ ሲሆን የመርማሪ ቡድን አባለት ምርመራ ለማድረግ ወደ ኦሮሚያ ክልለ ምእራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማ ግብረ አበሮቻቸውን ለመያዝ ልከናል” ብለዋል ::

ፖሊስ ከዚህ ቀደም በዋለው ችሎት ከጋዜጠኞች የተወሰዱ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ለምርመራ ወደ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ የመላክ ስራ መጠናቀቁን እና ከኤጀንሲው በጋዜጠኞቹ ላይ ተጨማሪ “የቴክኒክ ማስረጃዎችን” እንዲልክ እየጠበቀ መሆኑን ተናግሮ ነበር።

የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ፖሊስ ከዚ ቀደም እየሰራው ነው ያለውን ስራ ነው አሁንም እየተናገረ ያለው ለየት ያለ የተናገረው ነገር ቢሆን መርማሪ ቡድኑ ወደ ኦሮሚያ ክልል መሄዱ ብቻ ነው በማለት ተከራክረዋል:: ስለዚ ደንበኞቻችን በዋስ ተለቀው ክሳቸውን ይከታተሉ ሲሉ ፍርድ ቤቱን ተይቀዋል ::

የሁለቱን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤት የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ አድርጎ ለመርማሪ ፖሊስ 11 ተጨማሪ የምርመራ ቀን በመስጥ ተለዋጭ ቀጠሮ ለመጋቢት 20 2014 ሰቷል:: አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.