ዜና፦ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው በተጠረጠረበት ሁከትና ብጥብጥ ማነሳሳት ወንጀል ፖሊስ አስተያየት እንዲሰጥ ትእዛዝ ተሰጠ

በማህሌት ፋሲል

አዲሰ አባባ ፣ ሰኔ 3/ 2014፦ የአልፋ ቲቪ የዩትዩብ ቻናል መስራች እና ባለቤት ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው የተጠረጠረበት ወንጀል ጉዳዩ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሸፈን አለበት ወይስ የለበትም በሚለው ጉዳይ ላይ ፖሊስ አስተያየት እንዲሰጥ የ5 ቀን ተጨማሪ ቀን  ዛሬ ተሰቷል።

ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ግንቦት 27 ቀን፣ 2014 ዓ.ም ከሰዓት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ቅዳሜ ግንቦት 20፤ 2014 ፍርድ ቤት ቀረቦ ፖሊስ “ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል” ጠርጥሬዋለሁ ሲል ለየፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ክስ አቅርቦ ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀን እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ፍርድ ቤቱም መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን የምርመራ ቀናት በሁለት ቀንሶ 12 ቀናትን ፈቅዷል። ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገን ክርክር ካዳመጠ በኋል በመጪው ሰኔ 2፤ 2014 በሚኖረው ቀጣይ ቀጠሮ ፖሊስ በተሰጡት የምርመራ ቀናት ያከናወናቸውን ተግባራት አንዲያቀርብ ትእዛዝ አስተላልፏል።

ሆኖም ፖሊስ በትላንትናው እለት (ሰኔ 2) በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በዋለው ችሎት ጋዜጠኛ በቃሉ የህዝብን ደህንነት አደጋ ላይ በሚጥል ወንጀሎች ተጠርጥሯል ሲል ከሷል፤ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠውም ጠይቋል። የጋዜጠኛው ጠበቃ ጠበቃ አቶ ታደለ ገብረ መድህን ከፖሊስ ጋር ባደረጉት ክርክር በበኩላቸው የጋዜጠኛ በቃሉ ጉዳይ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሸፈን እንዳለበት ጠቅሰው፤ ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ ተጨማሪ ቀናት እንዳይሰጥ መከራከሪያ አቅርበው ነበር።

ፍርድ ቤቱ የጋዜጠኛው ጉዳይ መታየት ያለበት በመገናኛ ብዙሀን አዋጅ ነው ወይስ በወንጀል የሚለውን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠ ቢሆንም በዛሬው ችሎት ጋዜጠኛው በምን መከሰስ እንዳለበት ብይን ሳያስተላለፍ ቀርቷል ፤ይልቁንም ፖሊስ አስተያየቱን እንዲሰጥ 5 ተጨማሪ ቀን ሰጥቷል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.