ዜና፡ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ በ50,000 ብር ዋስ እንዲለቀቅ አዘዘ

አዲስ አበባ መጋቢት 27፣ 2014 የተራራ ኔትወርክ ኦንላይን ሚዲያ ዋና አዘጋጅ የሆነው ታምራት ምንም አይነት ክስ ሳይመሰረትበት 117  ቀናት ክስ ሳይመሰረትበት እና የዋስትና ጥያቄው ሳይፈቀድለት  በፖሊስ ቁጥጥር ስር ቆይቷል።

መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን ፊንፊኔ ዙሪያ በሚገኘው ገላን ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች በጋዜጠኛ ታምራት ላይ አቃቤ ህግ በ15 ቀናት ውስጥ ክስ እንዲመሰርት  ማዘዙ ይታወሳል። በተጨማሪም ዳኞቹ አቶ ታምራት በኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን ፊንፊኔ ዙሪያ ወደሚገኘው ሰበታ ከተማ ዳለቲ ፖሊስ ጣቢያ እንዲዘዋወር ውሳኔ አስተላልፎ ነበር።

በመቀጠልም የመከላከያ ቡድኑ ደንበኛቸው በዋስ እንዲለቀቅ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዋስትና ጥያቄውን ከመረመረ በኋላ ለመጋቢት 15 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ዳኞቹ መርማሪ ፖሊስ የምርመራ ውጤቱን እንዲያመጣ ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር።

ዛሬ በዋለው ችሎት መርማሪ ፖሊስ ያቀረባቸውን ሰነዶች በሙሉ ከመረመረ በኋላ ዳኞቹ አቶ ታምራት በ50,000 ብር ዋስ እንዲለቀቁ ብይን ሰጥተዋል። ነገር ግን በሌሎች የፍርድ ሂደቶች እንደሚስተዋለው ፖሊስ ፍርዱን ይግባኝ ለማለት ማቀዱ በጋዜጠኛው ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እና ምርመራ ለመቀጠል ማሰቡ ግልጽ አይደለም።

በየካቲት ወር ፖሊስ ታምራትን ክስ ለመመስረት የፈለገውን የክስ ዝርዝር የያዘ ገላን ለሚገኘው ፍርድ ቤት ባለ ሁለት ገጽ የክስ መዝገብ ያቀረበ ሲሆን ቀሪዎቹ የምርመራ ሂደቶች የአቶ ታምራትን የስልክ መዝገቦች እና የኮምፒዩተር ማስታወሳች  ለፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ገልጾ ነበር።

አቃቤ ህግ በአቶ ታምራት ላይ ክስ ሊመሰርትባቸው ከፈለጉት ውንጀላዎች መካከል “ለአንድ አመት በዘለቀው ጦርነት የህወሀትን ጥቅም የሚያራምዱ መረጃዎችን ሲያሰራጭ ነበር”፣  “ስለ ጦርነቱ ሂደት የተሳሳተ መረጃ እያሰራጭ ነበር” እና “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሆን ብለው የሀገሪቱን ስም በሚያጠፋና ወደ ዝቅተኛ ደረጃ በሚያወርድ መልኩ እየሰሩ ነው” የሚሉ መረጃዎች አሰራጭቷል የሚሉ ይገኙበታል ። መርማሪ ፖሊስ ታምራት ህወሓት እና ኦነግ በጦርነት ካደረሱት  ዉድመት ጋር የሚመጣጠኑ ወንጀሎች ፈጽሟል ማለቱ አይዘነጋም።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.