ዜና፡ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዋና ክፍል ኃላፊ ተገደሉ

ሟቹ ኮማንደር ዋጋው ታረቀኝ። ምስል፡- የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10/ 2015 ዓ.ም፡ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ዋጋዉ ታረቀኝ ከምሽቱ 6፡00 ሰዓት አካባቢ ጸጥታ በማስከበር ላይ በነበሩበት ወቅት በጥይጥት ተመተው መገደላቸውን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቀ።

የክልልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮማንደሩ ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸዉ ማለፉን ጠቅሶ ለህዝብና ለሀገር ሲሰሩ መስዕዋት ሆኗል ሲል ገልጿል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የምትገኘው የሸዋ ሮቢት ከተማ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት ሃሙስ መስከረም 01 ቀን ማምሻውን መገደላቸው ይታወሳል። ከንቲባው ከመኪና ላይ ወርደው ወደ ቤታቸው ሊገቡ ሲሉ ነው በጥይት የተገደሉት፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.