ዜና፡ የሸዋ ሮቢት ከንቲባ ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት ተገደሉ

አቶ ውብሸት አያሌው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27/2014፡- የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ትላንት ማታ ከምሽቱ 3 ስዓት ገደማ አካባቢ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት ተገደሉ በማለት የከተው አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት አስታወቀ።

ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት “የተሰጣቸውን የህዝብ አደራ ለመወጣት ውሎአቸውን በስራ ተጠምደው ለእረፍት” ወደ ቤታቸው ከመኪና ላይ ወርደው ሊገቡ ሲሉ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰባቸው ጥይት መገደለቸውን ቢሮው በተጨማሪ አስታውቋል።

ቢሮው ያወጣው መግለጫ እንዳለው “አቶ ውብሸት ወደ ሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር በስራ ኃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት በቀወት ወረዳ አስተዳደር በተለያዮ ተቋማት በባለሙያነትና በስራ ኃላፊነት ህዝብን በለጋ የወጣትነት ጊዜያቸው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።”

ከዚህም በተጨማሪ ተቀዳሚ ከንቲባ ቀብሩም ዛሬ በሸዋሮቢት ከተማ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቀኑ 6 ስዓት ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት የስርአተ ቀብራቸው ይፈጸማል “እንደ አንድ የህዝብ አደራ እንደተቀበለ አመራር እና እንደ ተወላጅ ከተማዋ የሚገባትን እድገትና ማዕረግ እንድታገኝ እንዲሁም ነዋሪዎቿ ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ በከፍተኛ ቁጭት እየሰሩ የሚገኙ ወጣት አመራር ነበሩ” በማለት የከተው አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በማለት በተጨማሪ ገልጿል።

ነዋሪነቱን በዚሁ ከተማ እንደሆነ ጠቅሶ ለአዲስ ስታንዳርድ ስሙ እንዳይገለፅ አሳስቦ “ምንም እንኳን እርግጠኛ ባልሆንም ከጥቂት ወራት በፊት መንግስት በወሰደው እርምጃ ቀደም ሲል ፋኖዎች እንዲታሰሩ ከንቲባው እጁ አለበት በሚል ማህበራዊ ትስስርን ጨምሮ በተለያዮ መንገዶች ሰዎች ማስፈራሪያ ያደርጉ ነበር” ሲል ተናግሯል።

ስሜ አይጠቀስ ያለው አዲስ ስታንዳርድ ያናገረቺው ሌላኛው የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪ “ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጀምሮ አብረን ተምረናል። ለሰዎች ጥሩ አሳቢ ነበር፤ ማንንም ለመጉዳይ አያስብም፤ ለሃገር የሰራ ነው” ሲል የተናገረ ሲሆን “ምን አልባት ከዚህ በፊት ታስረው ያልተፈቱ ፋኖዎች እሱ ነው ያሳሰራቸው በሚል ማስፈራሪያ ይደርሰው እንደነበር አቃለሁ። እርግጠኛ መሆን ባይቻልም ግድያው ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል” ብሏል።

አዲስ ስታንዳርድ ሰኔ 282014 . በሸዋ ሮቢት ከተማ የተካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት መድረሱን መዘገቧ ይታወሳል።

በወቅቱ የከተማዋ ነዋሪዎች   ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት የከተማው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሐሙስ ሰኔ 21 ቀን 2014 ዓ.ም በወለጋ የአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ በማውገዝ መንግስት ህገ መንግስታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ እና በሀገሪቱ ውስጥ ህግና ስርዓት እንዲሰፍን  በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀው እነደበር

የአቶ ውብሸት የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ በሸዋሮቢት ከተማ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቀኑ 6 ስዓት ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ይፈጸማል።

አቶ ውብሸት አያሌው ባለትዳር እና የአንድ ሴትና አንድ ወንድ አባት ነበሩ ። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.