ዜና ፈጠራ: በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የ8ኛ ክፍል ተማሪ በሰራው የፈጠራ ስራ 16 ነዋሪዎችን የመብራት ሀይል ተጠቃሚ ማድረግ ቻለ

አዲስ አበባ: ግንቦት 18/2014 – በቦረና ዞን ዋጪሌ ወረዳ ዌቢቲ ቀበሌ ነዋሪ ነው። የስምተኛ ከፍል ተማሪ አደን ሁሴን፤ በፈጠራ ስራው የቀበሌውን ነዋሪዎች የመብራት ሀይል ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡

ተማሪ አደን ሁሴን ባዮጋዛ በማዘጋጀት፣ ሽቦና ፕላስቲክን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት ችሏል፡፡

በዚህም ከራሱ አልፎ ለ16 የቀበሌው አባወራዎች መስመር በመዘርጋት የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚ አድርጓቸዋል፡፡

በአካባቢው የሚከናወነውን የባዮ ጋዝ አሰራርን መነሻ በማድረግ የራሱን የፈጠራ ችሎታ በማከል ውጤታማ ስራ ማከናወን መቻሉን ተማሪ አደን ተናግሯል።

በፈጠራ ስራው በወር አንድ ሺህ 600 ብር ገቢ እያገኘ እንደሆነም ተናግሯል፡፡

የተማሪ አደን ወላጅ እናት ወ/ሮ መሱ ሁሴን አደን ስድስተኛ ልጃቸው ሲሆን ነገሮችን የመመራመርና አዲስ ነገሮችን የመሞከር ዝንባሌ እንደነበረው ገልጸዋል።

የዞኑ የውኃና ኢነርጂ ፅ/ቤትም ለፈጠራ ስራው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ጨምሮ አስፈላጊው ድጋፍ ለተማሪ አደን ሁሴን ይደረጋል ብለዋል።

ዘገባው የኢ.ፕ.ድ ነው።

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.