ዜና:- መንግስት በቤንሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ንፁሃንን በህይወት ያቃጠሉ የጸጥታ ሃይሎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ

በመተከል ዞን የጸጥታ ሃይሎች ሰላማዊ ዜጎችን በህይወት ሲያቃጥሉ

ሲያኔ መኮንን

 አዲስ አበባ መጋቢት 03/2014  ፣ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ሠዎችን በእሳት ሲያቃጥሉ የሚያሳየው በማህበራዊ ድረ-ገጾች በሰፊው ተሰራጭቶ የነበረው ተንቀሳቃሽ ምስል ቦታው  ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ መሆኑን የፌደራል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ተቋሙ “ይህ ድርጊት ከኢትዮጵያዊነት ባህል፣ እሴትና ከማንኛውም የሰብአዊነት እሳቤ ያፈነገጠና እጅግ አሰቃቂ ወንጀል ነው።” ብሏል። 

የተጎጂዎችን ማንነት በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያዎች ብዙ መላምቶች እየተናፈሱ ሲሆን መንግስት ድርጊቱ የተፈፀመበትን ቦታ ቢለይም የተጎጂውን ማንነት እንዲሁም ተጨማሪ ማብራሪያ ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል። የፌዴራል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ እና ሚኒስትር ዴኤታዋ ወይዘሮ ሰላማዊት ካሳን ለማናገር የተደረገው ጥረት አልተሳካም።

በተንቀሳቃሽ ምስሉ የድርጊቱ ፈጻሚዎች የአንድን ሻለቃ ሞት አየተበቀሉ እንደሆነ ሲነጋገሩ ተደምጠዋል። ወንጀለኞቹ አጸያፊ ቃላት ሲለዋወጡ እና ሰብአዊነት የጎደላቸው ቋንቋዎችን ሲናገሩ ተደምጠዋል፤ ከተጎጂዎቹ አንዱ በእሳት በሚቃጠልበት ወቅት በህይወት እንደነበር ይታያል።

የአምስት ደቂቃ ርዝመት ያለው ተንቀስቃሽ ምስል ከአማራ እና ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የተውጣጡ የጸጥታ ሃይሎች እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ብሎም ሲቪል የለበሱ በርካታ ሰዎች ይታዩበታል። 

ባለፈው መስከረም ወር ላይ የሌሎች ክልሎች ልዩ ሀይሎች በተለይም ከአማራ ክልል ወደ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መሰማራታቸው ይታወሳል። በተጨማሪም፣ የጋምቤላ፣ የሲዳማ እና የደቡብ ክልል ልዩ ሃይሎች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡላን ወረዳ ላይ መሰማራታቸው አይዘነጋም።

 ከክልሎች የተውጣጡ ልዩ ሃይሎች የሠላም ማስከበር ተልዕኮ እያከናወነ መሆኑን የገለጹት የሰላም ግንባታና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት አልቦሮ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባለበት አካባቢ ሰላምን ለማስፈን የጸጥታ አካላት ርብርብ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። የቤኔሻንጉል ክልል መንግስትም የአማራ ልዩ ሃይል ወደ መተከል ዞን መሰማራት “የጁንታ ተላላኪዎችን” እና “የህወሓትን ርእዮተ አለምና የአስተሳሰብ የሚያራምዱ ርዝራዦችን” ለማጥፋት መደረጉን በወቅቱ አብራአቶ ነበር። 

የፌደራል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ጠዋት በሰጠው መግለጫ ድርጊቱን በፅኑ በማውገዝ ወንጀለኞችን ለህግ እንደሚያቀርብ አስታውቋል። መግለጫው በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ህገወጥነትንና በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቆጣጠር የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የሚያደርጉትን ጥረት ጠቅሷል። መግለጫው “የየንፁሃን ዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ ሰዎችን መንግስት አይታገስም” ሲል አስጠንቅቋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.