ዜና: 31 የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞከራሲ ፓርቲ አባላት አራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የግዜ ቀጠሮ ችሎት ቀረቡ

ማህሌት ፋሲል 

አዲስ አበባ መጋቢት 01 2014:- ባሳለፍነው ቅዳሜ በፓሊስ ቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት እና በልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ የባልደራስ ፓርቲ አባላት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ክርክር አደረጉ:: 

የካራማራ የድል በአልን ለማክበር የካቲት 26 ቀን 2014 ዓም ድላችህን ሃውልት አከባቢ የተገኙ የፓርቲው አባላት በፖሊስ ወደ በዓሉ አንዳይገቡ ከተደረጉ በኋላ የታሰሩት 31 የሚሆኑ አባላት በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ዛሬ በዋለው  ችሎት የካቲት 26  2014 የካራማራ የድል በአል በሚከበርበት ወቅት ህገመንግስቱ የማይፈቅደውን ባንዲራ ይዘው  ሁከትና ብጥብጥ ለማንሳት ሲሞክሩ ነው የያዝኩዋቸው እንዲሁም የባለስልጣናትን ስም እየጠሩ  ሲሳደቡ እና ሲያዋርዱ ነበር ያለው ፓሊስ የማጣራቸው ነገሮች ስላሉ የሰው ምስክር እና የሰነድ ማስረጃዎች ለማሰባሰብ 14  የምርመረ ቀን ይሰጠኝ ሲል ችሎቱን ጠይቋል ::

ጠበቆች በበኩላቸው በዚህ ጉዳይ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ቀርቦ እስከ ይግባኝ ድረስ ቀጠሮ ተሰቶበታል ስለዚ ይህ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለመመልከት ስልጣን የለውም ያሉ ሲሆን መታየትም ካለበት በታሰሩበት ወንጀሉ ተፈፀመበት በተባለው አካባቢ ባለው በፌደራል  የመጀመሪያ ደረጃ ልደታ ፍርድ ቤት ነው እንጂ አራዳ ፍርድ ቤት መታየት የለበትም በአንድ  ጉዳይ ሁለት ግዜ የግዜ ቀጠሮ ሊከፈት አይገባም ብለው ተከራክረዋል። 

“በአሉ በተከበረበት ወቅት የአዲስ አበባ መስተዳድር በአላቱ በሰላም መጠኛቀቁን መግለጫ አውጥቶ ባለበት ሁኔታ ፖሊስ ሁከትና ብጥብጥ ተነስቷል ማለቱ እነዚህን ሰዎች ሆን ብሎ ለማሰር ካልሆነ በቀር ምንም የሚያስጠጥር የወንጀል ተግባር በወቅቱ አልተፈፀመም” ሲሉም ሞግተዋል :: አክለውም ባለስልጣናት ተሰድበዋል ለተባለው ባለስልጣናቱ ተሰድበናል ብለው ክስ መስረት ይችላሉ እንጂ ፖሊስ በራሱ አነሳሳሽነት ስድብና መዋረድ ተግባር ተፈፅሟል ብሎ ምርመራ ማድረግ አይችልም እንደዚ ለማድረግ የሚያስችል የህግ መሰረት የለውም በማለት ተከራክረዋል ::

የሁለቱን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤት የሁለቱን ክርክር መርምሮ በክርክሩ ላይ ብይን ለመስጠት ለፊታችን ሰኞ 05/ 07/ 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል:: አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.