ዜና፡ የብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ቤተሰቦች የት እንዳሉ ማወቅ አልቻሉም

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014- የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ትላንት  ከጠዋቱ 5:15 ሰዓት አካባቢ ጓደኛቸውን ለማግኘት እንደሄዱ ወደ ቤት አለመመለሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ሃይሌ አረጋግጠዋል።

ወ/ሮ መነን ለቢቢሲ አማርኛ እንደገለፁት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ በመሄድ ባለቤታቸው የት እንዳለ ለመጠየቅ ጥረት ቢያደርጉም “እሱ በቁጥጥር ስር አልዋለም” ተብያለሁ ብለዋል።

የትግራይ ታጣቂዎች በታህሣሥ ወር የአማራ ክልልን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት በክልሉ ሰፊ ጥቃት ሲያደርሱ በነበረበት ወቅት የክልሉ ልዩ ሃይል አዛዥ ነበሩ። ነገር ግን የካቲት 10፣ 2014 ዓ.ም ብ/ር ጄኔራሉ ከኃላፊነታቸው ተነስተው ለክልሉ ፕሬዚዳንት ይልቃል ከፋለ ( ዶ/ር)  የጸጥታ አማካሪ ሆነው የተሾሙ ቢሆንም ሹመቱን ሳይቀበሉት ቀርተዋል። 

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ባለፉት ሳምንታት በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን በመቅረብ የፋኖን አደረጃጀት ጨምሮ የአማራ  ክልል የጸጥታ መዋቅርን “ለማዳከም” የፌደራል መንግስት እየሰራ መሆኑን እና  እየተወሰደ ያለውን ዕርምጃ  ሲተቹ ቆይተዋል። አንዳንድ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ወታደራዊ ክህሎትና ፍላጎት የላቸውም እንዲሁም በትግራይ ሃይሎች ላይ የተሳካ ወታደራዊ ጥቃት እንዳይሰነዘር  የሴራ አካል ናቸው ሲሉም ተደምጠዋል።

 እንደ ባለቤታቸው አገላለፅ፣ ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ከመኖርያቸው ባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ የመጡት እግራቸው ውስጥ የቀረ ጥይት በሚመለከት የህክምና ክትትል ሊያረጉ ነው። ጨምረውም “እስሩን ለምዶታል ግን ጤናው ያሳስበናል” ብለዋል።

ስለ ጀኔራሉ…

ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ የአማራ ክልል ልዩ ሀይል የመሩ ሲሆን በሰኔው 2011 የአማራ ክልል አመራሮች ግድያ በተገናኘ ከሌሎች 52 ሰዎች ጋር ለእስር ተዳርገው ነበር። ሆኖም ግን በታኅሣሥ 9 2012 ክሳቸው (ኮሎኔል አለበል አማረ፣  ኮሎኔል ባምላክ ተስፋ እና ኮማንደር ጌትነት ሽፈራው ጨምሮ) ተሰርዞ በሐምሌ 2013 ወደ ቀድሞ አመራርነት ቦታቸው ተመልሰዋል። 

ጀነራሉ በመፈቀለ መንግስት እንቅስቃሴ ተከሰው ከብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ጋር በ2001 ታስረው እንደነበሩ ይታወሳል። ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ከአስር አመት እስር ከሚሆን ጊዜ ቡኃላ በ2010 የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ ተከትሎ መፈታታቸው አይዘነጋም ። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.