ዜና፡ በሀረሪ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ የአፋን ኦሮሞ ጋዜጠኛ እና አርታኢው ሙሀይዲን አብዱላሂ ታሰረ

 በእቴነሽ አበራ

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 9፣ 2014 ዓ.ም- በሀረሪ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ የአፋን ኦሮሞ ጋዜጠኛ እና አርታኢ የሆነው ሙሀይዲን አብዱላሂ ማክሰኞ ግንቦት 2 ቀን በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነገረ ። ከ11 አመት በላይ በጋዜጠኝነት ያገለገለው ሙሀዲን በቁጥጥር ስር የዋለው ልጅ መውለዱን ተከትሎ የአመት ፈቃድ ከወሰደ ከአንድ ቀን  በኋላ  እንደሆነ ባለቤቱ ሄለን ጀማል ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግራለች።

በዚያው የመገናኛ ብዙሃን ተቋም ጋዜጠኛ የሆነችው ሄለን ባለቤቷ ከሚሰራበት ቢሮ እንደተወሰደ  ተናግራለች።  “ከአራስ ልጄ ጋር ተቀምጠን እያለ  ፖሊሶች በፓትሮል መኪኖች መጥተው ቤታችንን ከበቡት።  ባለቤቴን ሊይዙ እንደመጡ ነገሩኝ። ምክንያቱን ስጠይቅ በስልክ ሊያገኙት እንዳልቻሉ ሲነገሩኝ ስልክ ደወዬለት አነጋገሩት።” ስትል የነበረውን ሁኔታ አብራርታለች።

ሄለን እንዳለችው ከሆነ ፖሊሶቹ መኖሪያ ቤቱን ሲፈፈትሹ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አልነበራቸውም። አክላም ” ከዛ በኃላ ወደ ቢሮ ሄደው በቁጥጥር ስር አዋሉት” አለች። 

መሀይዲን በፖሊሶች ከተወሰደ በኃላ እስከ ሁለተኛው ቀን ድረስ የት እንዳለ ማወቅ እንዳልቻለች ያወሳችው  ሄለን፣ ”ፍርድ ቤት የቀረበው ሀሙስ ቀን ነበር፣ የተከሰሰውም ፌስቡክን ተጠቅሞ ህዝብን በመንግስት ላይ በማነሳሳት ነው ” ብላለች። የፌስቡክ ፅሁፈቹ በጎንደር ከተከሰተው ክስተት ጋር እንደሚገናኝ አስረድታለች። አቃቢ ህጉ አስራ አራት ቀናት ለምርመራ እንደጠየቀም ተናግራለች። 

የሙሀዲን የቅርብ አለቃ የሆነው ሙራድ መሀመድ  ስለ ጉዳዩ እንደማያውቅ እና የአመት ፍቃድ ላይ መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግሯል። የሀረሪ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ አመራሮችን ለማናገር የተደረገው ጥረት አልተሳካም። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.