ዜና፡ በጋምቤላ ከተማ ንጹሐን በጸጥታ ሀይሎች መገደላቸው ተሰማ ፣ ኢሰመኮ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ አሳሰበ

በሲያኔ መኮንን

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 10/2014 ፦የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች  እጆቹ ወደ ኋላ የታሰረ ሰው ላይ በተደጋጋሚ ሲተኩሱ የሚያሳዩ አስደንጋጭ ቪዲዮ በትላንትናው እለት በበርካታ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተለቋል ። ፊልሙ የተቀረፀው በጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ መሆኑ የተነገረ ሲሆን የጋምቤላ ነፃ አውጪ ግንባር/ጦር እና መንግስት ሸኔ ብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሰ) በከተማዋ ጥምር ኦፕሬሽን አካሂደናል ካሉ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት “እኛ የምናውቃቸው አሥራ አንድ ሰዎች ተይዘዋል። በሕይወት የተረፈው አንድ ሰው ብቻ ነበር ። በቪዲዮው ያየኸው ወጣት ከቤቱ ተወስዶ በጥይት ተገድሏል። በጋምቤላ ከተማ እህቱ ነበረች ያሳደገችው ። ዕድሜውን በሙሉ እዚህ ኖሯል።”  ሲል አክሎም “ደህንነቴን አደጋ ላይ ስለሆነ ተጨማሪ መረጃ ማሳወቅ አልችልም። ብዙ ሰዎች ተገለዋል። ዓለም እንዲያውቅ እንፈልጋለን” ብሏል።

ሌላው ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ  የጋምቤላ ከተማ ነዋሪ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች “የሸኔ አባላትን ፍለጋ” መኖሪያ ቤቶችን እየፈተሹ እንደሆነ  ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግሯል።

የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ማክሰኞ ጠዋት ባወጣው መግለጫ በጋምቤላ ነጻ አውጪ ግንባር  እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀው  የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት  በመንግሥት ኃይሎች ጋር መካከል የተኩስ ልውውጥ መደረጉን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ “የፀጥታ ኃይሎች ሕይወት ሊያጠፋ ከሚችል ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ መቆጠብ እና በፀጥታ ኃይሎች የተወሰዱ ሕገ ወጥ ተግባራት ላይ በአስቸኳይ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል” ሲል አሳስቧል ።

ማክሰኞ ከሰአት በኋላ የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽሕፈት ቤት የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ወይም (መንግስት “ሸኔ” ብሎ የሚጠራቸው) እና የጋምቤላ ነጻነት ሰራዊት/ ግንባር በጋራ የታጠቁ ቡድኖች  ጋር ለሰዓታት ከተዋጉ በኋላ የጋምቤላ ከተማን ማረጋጋት መቻላቸውን አስታውቋል። መግለጫው አክሎም የቀሩትን የዓማጺያኑን ቡድን አባላት “ለማጽዳት” እና “ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት” ተጨማሪ እርምጃዎች መወሰዳቸውንም ገልጿል።” 

አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረቻቸው የጋምቤላ ከተማ ነዋሪ የ”ሸኔ” አባላት ናቸው የተባሉ ሰዎች መኖሪያ ቤት በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች  እየፈተሹ መሆኑን  ገለፀዋል። ነዋሪው በስፋት ስለተሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል እንዳልሰማ ቢናገርም ነገር ግን “05” በተባለ አካባቢ ተመሳሳይ ድርጊት እንዳየ ገልጿል። “የታጠቁ ቡድኖች አባል መሆን አለመሆኑን እርግጠኛ ባልሆንም አንድ ሰው በአንድ ፋርማሲ  ፊት ለፊት በጥይት እግሩን ተመቶ ወደ ሆስፒታል ሲወሰድ  አይቻለው” ያለ ሲሆን አክሎም  “የጥቃት ሰለባዎች የታጠቁ ቡድኖች አባላት መሆናቸውን መለየት አስቸጋሪ ነው፣ ነገር ግን የፀጥታ ኃይሎች ከእነርሱ በሚሸሽ ሰው ላይ በጥይት ይተኩሱ ነበር። ፀጉራቸው ሹሩባ የተሰሩ እና የአማርኛ ወይም የጋምቤላ ቋንቋ መናገር የማይችሉ በተለይም  ኦሮምኛ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች በጥይት ተገድለዋል። የመንግስት ሃይሎች በጥቃቱ ከፍተኛ ኪሳራ ስለደረሰባቸው በአደጋ የተጎዱ ሰዎችን ላይ ጥይት በዘፈቀደ ይተኩሱ ነበር” ብሏል።

አክሎም የከተማይቱን ወቅታዊ ሁኔታ ሲገልጽ ” አሁንም ቢሆን በጣም ውጥረት ነግሷል።  ቤታችንን ለቀን መሄድ አልቻልንም። የጥይት ድምጽ እየቀነሰ መጥቷል። ተጠርጣሪዎችን ከመገደል ይልቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቢወስዷቸው ይሻል ነበር” ሲል ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግሯል።.

የክልሉ መንግስት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ የከተማዋ ነዋሪዎች ”በአካባቢያቸው የተደበቁትን’ የታጣቂ ቡድኖቹን አባላት ለፀጥታ ሃይሎች እንዲሳውቁና ከምሽቱ 2 ሰዓት በኋላ ከቤት እንዳይወጡ አሳስቧል።

የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ፕሬስ ሴክሬተሪያት ቢሮን ለማነጋገር የተደረገው ሙከራ አልተሳካም። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.