ዜና ፈጠራ፡ ነዳጅን በቀላሉ ማምረት የሚያስችል ቴክኖሎጂ በመካኒካል ምህንድስና ተማሪዎች መሰራቱ ተገለፀ

በብሩክ አለሙ

አዲስ አበባ፡ ሰኔ 10/2014 ዓ.ም ፡- በጅማ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የመካኒካል ምህንድስና ተመራቂ ተማሪዎች ነዳጅ ማምረት የሚችል ማሽን መስራታቸውን የጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ

ያገለገሉ ፕላስቲኮች በመሰብሰብ በሙቀት አማካኝነት ፓይሮሊሲስ በተሰኘ ሂደት የነዳጅ ምርትን  ለማምረት የተቻለ ሲሆን እስካሁን በተደረገው ሙከራ በሰዓት ውስጥ ሦስት ኪሎ ግራም ፕላስቲክ በመጠቀም ሁለት ሊትር ነዳጅ ማምረት የተቻለ በመሆኑ ወደፊት በስፋት ከተሰራበት ከዚህ በላይ ማምረት እንደሚችል ተመራቂ ተማሪዎቹ ገልፀዋል፡፡

ይህ ቴክኖሎጂ ሀገሪቱ ያለባትን የነዳጅ እጥረት የሚቀርፍ በመሆኑ ትልቅ አስተዋፅዖ ከማድረጉም ባሻገር በሙቀት አማካኝነት የሚያዘጋጀው የነዳጅ ማምረቻ ማሽኑ በየትኛውም ቦታ በቀላሉ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን አካባቢን ሊበክሉ የሚችሉ የፕላስቲክ አይነቶችን በመጠቀም ለአገልግሎት በማዋል የአካባቢን ውበት የመጠበቅ ፋይዳም ይኖረዋል ተብሏል፡፡

የነዳጅ ምርቱ ለጀነሬተር ፣ ለቀላል ተሸከርካሪዎችና ለቤት መገልገያዎች ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ተመራቂ ተማሪዎቹም ከአምራች ሀይሉና ከተጠቃሚው ጋር በመቀናጀት ማሽኑን በቴክኖሎጂ ማጎልበት እንደሚገባና ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ እንሰራለን ያሉ ሲሆን ከዩኒቨርሲቲው ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የመካኒካል ምህንድስና የፕሮጀክቱ የቡድን አማካሪ የሆኑት መምህር አብርሃ ካህሳይ የተማሪዎችን ጥረት አድንቀው ”ከዩኒቨርሲቲው አስፈላጊው  እገዛ እየተደረገላቸው ሲሆን ይህንን ትልቅ ፕሮጀክት የተፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ድጋፋችን ይቀጥላል” ብለዋል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.