አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9/2015 ዓ.ም፡ በኩዌት አንዲት ኢትዮጵያዊትን ጨምሮ በሰባት ሰዎች ላይ ባለፈው ረቡእ የተፈጸመውን የስቅላት የሞት ቅጣት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሙሽን አወገዘ።
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ሊዝ ትሮሴል ግድያው “ዘግናኝ” ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡ ከተጎጂዎቹ መካከል አራት የኩዌት ዜጎች – ሶስት ወንድ እና አንዲት ሴት ፣ አንዲት ኢትዮጵያዊት ፣ አንድ ፓኪስታናዊ እና አንድ የሶሪያ ሰው እንደሚገኙበትም መግለጫው አስፍሯል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ውስጥ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ሀገራት በአለም አቀፍ ደረጃ የሞት ቅጣት እንዲቆም ጥሪ ካቀረቡ ከጥቂት ቀናት በኋላ የተፈጸመው የሞት ፍርድ እጅግ በጣም አሳዛኝ እርምጃ መሆኑንም በመግለጫው ተመልክቷል።
ከ 1960 ጀምሮ ኩዌት በአብዛኛው ከግድያ ወይም ከአደንዛዥ እጽ ጋር በተያያዘ ወደ 80 የሚጠጉ ሰዎችን በሞት ፍርድ እንደቀጣች ያስታወሰው መግለጫው አገሪቱ የሞት ቅጣት ፍርድ ትግበራን ከቀጠሉት 38 ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን አፅንዖት በመስጠት መሰል እርምጃዎችን እንዲታቆም አሳስቧል።
“ኩዌት ሁሉንም ዓይነት ግድያ ማቆም አለባት፣ የሞት ቅጣት ላይ መደበኛ የሆነ እገዳ በማድረግ በሞት ፍርደኞችን መታደግ ይኖርባታል” ሲል መግለጫው አስምሮበታል። ኮሚሽኑ የኩዌት ባለስልጣናት የሀገሪቱን ህጎች እና አሰራሮች ከአለም አቀፍ ህግጋቶች ጋር መጣጣም እንዳለባቸውም አሳስቧል. አስ