ዜና፦የአሜሪካ ኩባንያ ለአከባቢ ተስማሚ የሆነ የአፈርን ለምነት የሚያጎለብት ምርት በኢትዮጵያ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8/2015 ዓ.ም፦ አሜሪካው ጄ ኤስ ኤች ኢንተርናሽናል ኩባንያ ከኢትዮጵያዉ ጂግራ ኬሚካልስ ጋር በመተባበር አፔክስ-10 የተሰኘ ኦርጋኒክ የማዳበሪያ ማበልፀጊያ ምርት ለኢትዮጵያ ገበያ ለማቅረብ አየሰራ መሆኑን በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

እንደ መግለጫው አፔክስ-10 አሜሪካ ሰራሽ ሲሆን ለአካባቢ ተስማሚ እና የአፈርን ለምነት የሚያጎለብት ምርት ነው፡፡ መግለጫው በኢትዮጵያ ለንግድ አገልግሎት እንዲቀርብ የተፈቀደ መሆኑንም ገልፆ ምርቱ የማዳበሪያ ፍጆታን በእጅጉ የሚቀንስና ውሃ የማጠራቀም አቅሙ ከፍተኛ ነው ብሏል።

የግብርና ሚኒስትር ልዩ አማካሪ አቶ ስለሺ ጌታሁን እንዲሁም የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ተወካይ አቶ ግርማ አበራ በተገኙበት ማክሰኞ ህዳር 06 በተካሄደው የምርቱ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ምክትል ኃላፊ ፊዮና ኢቫንስ “ይህ ጅማሮ በአነስተኛ ደረጃ ላይ ላሉ ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች ፣ የንግድ አርሶ አደሮች አንዲሁም ለመላው የአገሪቱ ህዝቦች ከፍተኛ ጥቅም ያስገኛል” ሲሉ ተናግረዋል።

ስራውየተጀመረውየኢትዮጵያ ኩባንያ የጄኤስኤች አፔክስ-10 አለም አቀፍ ፈጠራ ምርትን በኢትዮጵያ የማከፋፈል እና የመሸጥ ልዩ መብት እንዲኖረው የሚያስችለውን ስምምነት ሁለቱም ኩባንያዎች በመስከረም 2013 ዓ/ም የተፈራረሙትን ስምመነትተከትሎ ነው።

“Apex-10 በመላው አፍሪካ እና በአለም ላይ ተሞክሮ ስራ ላይ የዋለ ሲሆን ምርቱ የማዳበሪያ እና የውሃ ፍጆታን እንደሚቀንስ ተረጋግጧል፡፡ የአየር ለውጥ ባለበት አንዲሁም የምግብና መዳበርያ አቅርቦት መስተጓጎል ባሉበት ቦታዎችን አስፈላጊ ነው” ሲል መግለጫው ገልጧል፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.