በብሩክ አለሙ @Birukalemu21
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25/2014 ዓ.ም፡- መንግስት በየወቅቱ የሚያደርገውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተከትሎ በሸቀጦች እና በመሰል ምርቶች ላይ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰደ የንግዱን ሴክተር እንዲመራ ሃገራዊ ሃላፊነት የተሰጠው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር አስታወቀ፡፡
ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የነዳግ ዋጋ ጭማሪ ተግባራዊ መደረግን ተከትሎ አንዳንድ የራሳቸውን ተጠቃሚነት ብቻ ለማረጋገጥ እቅድ ያላቸው ስግብግብ የህብረተሰብ ክፍሎች መሠረታዊ ሸቀጦች እና ምስል ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ላይ እንደገኙ ጠቅሶ ይህ ሃላፊነት የጎደለው ህገ-ወጥ ድርጊት አብዛኛው የሃገሪቱ የህብረተሰብ ክፍላችን በተለይም በዝቅተኛው የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚኖሩ ወገኖቻችን የእለት ፍጆታቸውን መሸፈን ወደ ማይችሉበት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ እያስገደዳቸው ይገኛል ብሏል፡፡
እክሎም ከዚህም በተጓዳኝ ይህ ህገ-ወጥ ድርጊት ትልቅ የኦኮኖሚ አሻጥር በመሆኑ ህዝቡ በሚመራው መንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ ስለሚያደርገው ድርጊቱ በምንም መልኩ ተቀባይነት አይኖረውም ሲል ገልጧል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት መስከረም 18/2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ቤንዚን በሊትር – 57 ብር ከ05 ሣንቲም ፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር – 59 ብር ከ90 ሣንቲም እንዲሁም ኬሮሲን በሊትር -59 ብር ከ90 ሣንቲም እንዲሆን መወሰኑን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ማሳወቁ ይታወሳል።
መንግስት በነዳጅ ላይ የዋጋ ጭማሪ ባደረገበት ማግስት ነጋዴውና የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች በህበተሰቡ ላይ የራሳቸውን ጭማሬ ሲያደረጉ መቆየታቸውን አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረቻቸው የተለያዩ የመዲናይቱ የማህበረሰብ ክፍሎች ተናግረዋል
መንግስት የነዳጅ ምርትን ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ መድቦ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት እየሸጠ ያለበት ዋጋ ኪሳራ ውስጥ እንዲገባ አስገድዶታል ያለው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ በህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ ገልፆ በቀጣይም ከሚመለከታቸው የክልል ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን መሰል እርምጃዎችን የሚወስድ ይሆናል ሲል አስስቧል፡፡
ከዚህ በፊት ተግባራዊ የተደረገው የነዳጅ ጭማሪ ምን ተፅዕኖ አስከተለ ?
ሚያዚያ ወር በተጨመረው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ተፅዕኖ እያሳደረብን ነው ሲሉ የትራንሰፖርት ተጠቃሚዎችና የታክሲ አሽከርካሪዎች መግለፃቸውን አዲስ ስታንዳር መዘገቧ ይታወቃል።
መንግስት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በእቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ በመግለፅ ቢያስጠነቅቅም በሰኔ ወር ላይ ሃሳባቸውን ለአዲስ ስታንደርድ ያካፈሉ የከተማዋ ነዋሪዎች የዋጋው ጭማሬ መኖሩንን በትራንፖርት ላይም ለከፋ እንግልት መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
መንግስት በነዳጅ ላይ የዋጋ ጭማሪ ባደረገበት ማግስት ነጋዴውና የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች በህበተሰቡ ላይ የራሳቸውን ጭማሬ ሲያደረጉ መቆየታቸውን አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረቻቸው የተለያዩ የመዲናይቱ የማህበረሰብ ክፍሎች ተናግረዋል፡፡ ይህም ድርጊት ቀድሞውኑ ለህዝቡ ከባድ የነበረውን የኑሮ ውድነት ይባስ እንዲያሻቅብ ማድረጉንም አክለው ገልፀዋል፡፡
የነዳጅ ዋጋ ጭማሪውን ተከትሎም አንዳንድ የትራንስፖረት አገልግሎት ሰጪ ያልተገባ የታሪፍ ጭማሪ በማድረግ ተጠቃሚውን ሲያንገላቱ መቆየታቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘገባለች፡፡ አሁን የደተረደውን ጭማሪን ተከትሎም ከተፈቀደው ውጭ የዋጋ ጭማሪ ሊደረጉ ስለሚችሉ ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግ እንደሚገባ አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረቻቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከታሪፍ ማስተካከያ በላይ ክፍያ የሚጠይቁ አገልግሎት ሰጭዎች ህግን ተላለፈው በሚገኙ አሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ቢያጠነቅቅም ማስጠንቀቂያውን ከቁብ ሳይቆጥሩት የነዳጅ ዋጋ መጨመርን ተከትሎ የትራንፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች ያልተገባ የታሪፍ ጭማሪ እንደሚያደርጉና ህጉ እየተተገበረ አለመሆኑን አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ያስረዳሉ፡፡ መንግሰት ያደረገው ማሻሻያያም ትልቅ ተፅእኖ አያደረሰብን ነው ሲሉ በመዲናዋ አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረቻቸው የትራንፖርት ተጠቃሚዎች አክለው ገልፀዋል፡፡
አዲስ ስታንዳርድ አዲስ አበባ ከተማ መገናኛ አከባቢ ተገኝታ የታክሲ ሹፌሮችን ያነጋገረች ሲሆን መንግስት በነዳጅ ላይ የዋጋ ጭማሬ ማድረጉን እንጂ ባለ ታክሲዎች ላይ የሚመጣውን ተፅዕኖ ከግንዛቤ ውስጥ አላስገባም ሲሉ ይናገራሉ፡፡ “የነዳጅ ጭማሬውን ምክንያት በማድረግ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሬ ተደርጎብናል፡፡ ጉዳዩ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ሊሰጠን ይገባል” ሲሉ በምሬት አክለው ገጸውልናል፡፡
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር ትላንት ባወጣው መግለጫ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በዚህ የኢኮኖሚ አሻጥር ውስጥ ተሳትፎ የሆኑ አካላት ከዚህ ህገ-ወጥ ድርጊት መታቀብ ይኖርባቸዋል ሲልም አክሎም አስጠንቅቋል፡፡ ሸማቹ የህብረተሰብ ክፍልም እንደነዚህ ያሉ ህገ ወጥ አካላትን ሲያስተውል ለሚመለከታቸው የንግድ ቢሮ አካላት ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደረግ ጥሪ አቅርቧል፡፡አስ