ዜና፣ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንኮበርን ጨምሮ በአራት ወረዳዎች ላይ የማሽላ ጢንዚዛ ወረርሽኝ ተከሰተ

በአሰፋ ሞላ @AssefaMolla6

አዲስ አበባ፣መስከረም 24/2015 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአንኮበር፣ ጣርማበር፣ ቀወት እና በረኸት ወረዳዎች የማሽላ ጢንዚዛ ወረርሽኝ መከሰቱን በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።የቀበሌና የወረዳ ባለሙያዎች ጢንዚዛው በሰብሉ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ፣ በባህላዊ ዘዴ በመልቀም፣ ማሽላውን በማወዛወዝና ጭስ በማጨስ እንዲሁም በኬሚካል የመከላከል ሥራ እየሰሩ መሆኑን የዞኑ የግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አበበ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡

እስካሁን 1 ሺህ 21 ሔክታር የማሽላ ሰብል ላይ ጢንዚዛ የተከሰተ ሲሆን፣ 966 ሔክታሩን በባህላዊ መንገድ፣ ቀሪውን 55 ሔክታር ደግሞ በኬሚካል የመከላከል ሥራ መሠራቱ ኃላፊው ገልፀዋል፡፡ኃላፊው ጢንዚዛው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሊስፋፋ እንደሚችል ግምት መኖሩን ጠቁመው ወደ አጎራባች ወረዳዎች እንዳይዛመት ሁሉም አርሶአደርና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያ የመከላከል ሥራው ላይ እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.