ዜና፡ የአልፋ ሚዲያ መስራቹ በቃሉ አላምረው በአፋጣኝ ከእስር እንዲፈታ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ተቋም የሆነው ሲፒጄ ጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5/2015 ዓ.ም፡- አለም አቀፉ የጋዜጠኞች ተቆርቋሪ ተቋም የሆነው ሲፒጄ የአልፋ ዩቲዩብ ሚዲያ መስራች የሆነው በቃሉ አላምረው በኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች አላግባብ መያዙን አስታውቆ በአፋጣኝ እንዲለቀቅ ጠይቋል። ሲፖጄ ነሃሴ 4 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በቃሉ አላምረውን በአፋጣኝ እንዲፈታ እና የፕሬስ ነጻነትን