ዜና፡ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መንግሥት ያልተገደበ የኃይል አጠቃቀም እንዲተገብር የሚያመቻች እንዳይሆን ሲል ኢዜማ አሳሰበ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 2/2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአማራ ክልል ከታወጀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ጋር የተያያዘ መግለጫ አውጥቷል። ኢዜማ ባወጣው መግለጫ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመንግሥት ያልተገደበ የኃይል አጠቃቀም እንዲተገብር የሚያመቻች እንዳይሆን ሲል አሳስቧል። በተጨማሪም አዋጁንም ተገን በማድረግ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች እንዳይፈፀሙ ሲል አስጠንቅቋል። አስቸኳይ