ዜና፡ የፌደራል መንግስቱ በአማራ ክልል በሚወስደው እርምጃ ምንም አይነት ተሳትፎ የለኝም ሲል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 8/2015 ዓ.ም፡- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ነሐሴ 7 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የፌዴራል መንግስት በአማራ ክልል ላይ እየወሰደው ባለው እርምጃ ‘የህወሓት ቀጥተኛ ተሳትፎ አለበት’ መባሉን አስተባብሎ ምንም አይነት አስተዋጽኦ እዳላደረኩም ሲል ገልጿል። ፅንፈኛ ሀይሎች ሲል በገለጻቸው አካላት ‘የህወሓት ቀጥተኛ ተሳትፎ አለበት’ በሚል የሚነዛው