ጥልቅ ትንታኔ፡ ከጦርነቱ በኋላ የትግራይ ክልል ፖለቲካ ምህዳር ምን ገፅታ ይኖረዋል? ቀጣዩ የትግራይ የፖለቲካ ትግል አቅጣጫ ምን ይሆን?
በሚሊዮን በየነ @MillionBeyene አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26/2015 ዓ.ም፡- በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መቋቋሙ ይታወቃል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ቆይታ ቢያንስ ስድስት ወራት ቢበዛ ደግሞ አንድ አመት እንደሚሆን ተደንግጓል። ይህም ማለት ግዜው ሲያልቅ በክልሉ ምርጫ ይካሄዳል ማለት ነው። ከጊዜያዊ አስተዳደሩ የስልጣን ግዜ ማብቃት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ አሸናፊ ሆኖ