ዜና: በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋና በዋግኸምራ ዞኖች በተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የጉድፍና የኩፍኝ በሽታ ተከሰተ

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ወለህ መጠለያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች። ምስል፡ የዋግ ኽምራ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

 

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 5፣ 20141 ዓም ፦በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በረኸትና ምንጃር ወረዳዎች እንዲሁም በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኙ ሁለት ማለትም በጭና እና ወይንሸት የተፈናቃይ ጣቢያዎች  የኩፍኝ በሽታ ተከስቷል። በተመሳሳይ፣ ባለፉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ በዋግኽምራ ዞን ወሌህ በተባለ የተፈናቃይ  ጣቢያ ላይ የጉድፍ በሽታ መከሰቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) አስታውቋል።.

ባለፈው ሳምንት በአዲስ ስታንዳርድ የቀረበ የዜና ትንታኔ በዋግ ኽምራ ተፈናቃዮች ላይ ያለውን የጤና ችግር ዘግቧል። በተለይ በአበርገሌ ወረዳ የወባ፣ የእብድ ውሻ በሽታ፣ ከፍተኛ የምግብ እጥረት እና አጣዳፊ ትውከት በሽታ በመከሰቱ ለስምንት ሰዎች ሞት ምክኒያት መሆኑን አዲስ ስታንዳርድ የዞኑን ጤና ጥበቃ ቢሮ በመጥቀስ ሪፖርት አድርጋለች።

የተባበሩት መንግስታት በዚህ ሳምንት ባወጣው ሪፖርት በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በቱርክ መንግስት በተገነባ የተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ በያዝነው አመት ሰኔ 22 ቀን በተደረገው ሁለገብ ኤጀንሲ ግምገማ ተፈናቃዮች በተጨናነቀ ሁኔታ እንደሚገኙ እና ከደረጃ በታች ያሉ መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዳገኘ አመልክቷል።

በዋግኽምራ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች 95,000 ተፈናቃዮች የኑሮ ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን እና 40,500 ተመላሽ ተፈናቃዮች በጊዜያዊ መጠለያ ወይም በፈራረሱ ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ ከመጠለያው ጣቢያ  እና ከምግብ ነክ ካልሆኑ አጋር ድርጅቶች  ገለጻ ለመረዳት ተችሏል

ጣቢያው ከሚያዝያ 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 3000 ተፈናቃዮችን እና ስደተኞችን በማስጠለል ላይ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን ሲሰጥ የነበረው ዕርዳታም በቋሚነት ሲደረግ እንዳልነበረ  እና በቂም እንዳልሆነም ተጠቅሷል። ሪፖርቱ አክሎም “ተንቀሳቃሽ የጤና አገልግሎት የለም” ያለ ሲሆን  አንድ የገላ መታጠቢያ  ብሎክ ብቻ እንዳለ ጠቅሶ  የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት እንደሌለም ተናግሯል። በመጸዳጃ ቤት እጦት ምክንያት ሰዎች ክፍት በሆኑ ቦታዎች እየተጠቀሙ መሆኑን አንስቶ ሁኔታውን “የጤና ጠንቅ” ነው ብሎታል። በቂ መጠለያ ባለመኖሩ ተፈናቃዮች እና ስደተኞች ለጤና እና ለጥበቃ ስጋት ተጋልጠዋል ሲልም የተ.መ.ድ ሪፖርት አመልክቷል።

በዚህ ዝናባማ ወቅት ሰዎች በአብዛኛው በኮንክሪት ወይም በባዶ መሬት ላይ ከላስቲክ በተሰሩ መጠለያ ውስጥ እየኖሩ መሆኑን ተናግሮ ምግብ፣ የጤና አገልግሎቶች፣ እንዲሁም ምግብ ነክ ያልሆኑ ነገሮች እንደ ፍራሽ እና የግል ንፅህና መጠበቂያ እንዲሁም አልባሳት በቅድሚያ ለተፈናቃዮቹ አስፈላጊ መሆናቸውንም ተገልጿል። በዋግኽምራ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች 95,000 ተፈናቃዮች የኑሮ ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን እና 40,500 ተመላሽ ተፈናቃዮች በጊዜያዊ መጠለያ ወይም በፈራረሱ ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ ከመጠለያው ጣቢያ  እና ከምግብ ነክ ካልሆኑ አጋር ድርጅቶች  ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በረኸትና ምንጃር ወረዳዎች እንዲሁም በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኙ ሁለት የተፈናቃ ካምፖች ውስጥ ማለትም በጭና እና  ወይንሸት ጣቢያዎች የኩፍኝ በሽታ እንደተከሰተ ሪፖርቶች አመልክተዋል። ከተመዘገቡት 44 ኬዞች (cases) ውስጥ በ13ቱ ሰዎች ላይ በሽታው እንደተገኘ ከሁለት ሳምንት በፊት በተደረገ በምርመራ ተረጋግጧል። በዋግኽምራ ዞን ወሌህ በተባለው የተፈናቃዮች ጣቢያም የጉድፍ በሽታ ካለፉት ሶስት ሳምንታት ወዲህ ተመዝግቧል። ከ380 ሰዎች በላይ በተደረጉ ጥናቶች በሽታው እንደተከሰተ የተረጋገጡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 30 በመቶው የሚሆኑት ከአምስት ዓመት በታች  ህጻናት መሆናቸው ተረጋግጧል።

ከግንቦት 2014 ዓ.ም ጀምሮም የወባ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን በክልሉ ከአንድ አመት በፊት ጀምሮ እስካሁን ከ540,000 በላይ ኬዞች (cases) ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን አብላጫዎቹ በማዕከላዊ ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች እንደተከሰቱም ተነግሯል። በሰኔ ወር የመጨረሻ ሳምንት የተመዘገቡት ሪፖርቶች ቁጥር ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነጻጸር የ29 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። የበሽታ አምጪ አስተላላፊ ትንኝ  ቁጥጥር አቅርቦት ውስንነት እና ዛንዚራን በአግባቡ አለመጠቀም ወባን ለመቆጣጠር ተግዳሮቶች እንደሆኑም ተገልጿል። እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ለትንኞች መራቢያ ምቹ የሆነ የውሃ ኩሬ የመፍጠር አቅም ስላለው ለወባ እና ለሌሎች የውሃ ወለድ በሽታዎች ከፍተኛ ተጋላጭነት እንደሚዳርግም ተመልክቷል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.