ትንታኔ፡ እርዳታ ፍለጋ ላይ ያለው የዋግ ኽምራ ጤና አገልግሎት እና የተፈናቃዮች የረሃብ ጭንቀት

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ወለህ መጠለያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች። ምስል፡ የዋግ ኽምራ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

በእቴነሽ አበራ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 1፣ 2014 ዓ.ም፦ በዋግ ኽምራ አስተዳደር ዞን ስር ያሉ ሶስት ወረዳዎች አበርገሌ፣ ዝቋላ እና ፀገበጅ እስካሁን በትግራይ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ያሉ ሲሆን በዚህም የተነሳ  ህዝቡ ለከፍተኛ ረሃብ፣ ድርቅ እና ለከፋ ችግር ተዳርጓል በማለት ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ቃለምልልስ ያደረጉ የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል። በተለይ አበርገሌ ወረዳ ወባ፣ የእብድ ውሻ በሽታ፣ ከፍተኛ የምግብ እጥረት እና አጣዳፊ ትውከት በሽታ በመከሰቱ ለስምንት ሰዎች ሞት ምክኒያት መሆኑን  የዞኑ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታወቋል።

የዋግ ኸምራ ዞን ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኪዳት አየለ እንደገለፁት የህክምና እርዳታ ለመስጠት ቃል የተገባ  ቢሆንም እስካሁን  ምንም አይነት እርዳታ እንዳልደረሳቸው ገልፀዋል። ጤና ቢሮው አክሎም በዚህ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ያው ቢሆንም ጉዳቱ እየተባባሰ መምጣቱን ገልፆ  “ዞኑ ለወባ የተጋለጠ በመሆኑና ወቅቱም አመቺ  በመሆኑ ከክልሉ ጤና ቢሮ እና ከክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አፋጣኝ እርዳታ እየጠየቅን  ነው “ብለዋል።

“በአሁኑ ጊዜ መጋዘን  ውስጥ ምንም የለንም። መደበኛው የምግብ አቅርቦት ቆሟል”

በዞኑ አበርገሌ ወረዳ ባልታወቀ በሽታ ህጻናትን ጨምሮ 9 ሰዎች መሞታቸውን ዶክተሩ አረጋግጠዋል። ዶክተሩ አክለውም አለም አቀፍ የህክምና መርማሪ ቡድን በትግራይ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ወደ ወረዳዎች መግባቱን የሚገልጽ ወሬ መስማታቸውን ገልፀው እስካሁን ምንም ማረጋገጫ አለመኖሩን ተናግረዋል። የሰቆጣ ከተማ ከ70,000 በላይ ተፈናቃዮችን ስትይዝ በትግራይ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ባለችው ዝቋላ ወረዳ ደግሞ  ከ18,000 በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ  የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አስታውቀዋል።

የዋግ ኸምራ ተፈናቃዮች የረሃብ ጭንቀት

በዋግ ኸምራ ዞን ስጋት መከላከልና የምግብ አቅርቦት ቡድን መሪ ወይዘሮ ዝናሽ ወርቁ ተፈናቃዮቹን በተመለከተ  “በአሁኑ ጊዜ መጋዘን  ውስጥ ምንም የለንም። መደበኛው የምግብ አቅርቦት ቆሟል” ብለዋል። 

እንደ ወይዘሮ ዝናሽ ገለጻ  የምግብ አቅርቦቱ ከቀድሞ ደቡብ ትግራይ ወደ ዋግ ኸምራ ዞን ስር ከተዋቀሩት ዛታ፣ ኮረም እና ኦፍላ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን አላካተተም። ከደቡብ ትግራይ ወደ ዋግ ኸምራ ዞን ስር የተመሰረቱት ወረዳዎች በመንግስት አመታዊ የምግብ ማሟያ ፕሮግራም ውስጥ እንዲካተቱ ተደርጓል። ወ/ሮ ዝናሽ ”መዋቅር ከሌላቸው ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች በዓመታዊው የምግብ ማሟያ ፕሮግራም ይሸፈናሉ ነገር ግን ጭንቀታችን ከእኛ ጋር ስለተዋቀሩ አዲስ ወረዳዎች ነው።  በበጎ ፈቃደኞች የሚሰጠው የምግብ ማሟያ በአሁኑ ጊዜም ቆሟል፣ ይህም በበኩሉ ትልቅ ክፍተት ፈጥሯል” ብለዋል። ከተጠቀሱት ወረዳዎች በግምት  ከ11,000 በላይ ተፈናቃዮችን እንደሚገኙ ገልፀዋል።

እንደ ዝናሽ ገለፃ ከሆነ ሰብአዊ እርዳታ ከደረሳቸው ወር ይሞላል። ” ተጋላጭ የሆኑት አራስ ልጆች፣ የሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም ተዛማች ያልሆነ በሽታ ያለባቸው ታማሚዎች ልዩ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ። በአሁኑ ሰአት በእጥረት ምክንያት ልዩ አጋዥ መድሃኒቶች ማቅረብ አልቻልንም። የከፋ ችግር እንዳይፈጠር እየፈራን ነው። ” በቀድሞ ጊዜ ደቡብ ትግራይ ውስጥ ከነበሩት ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ተወካዮች እየመጡ እርዳታ በየቀኑ ይጠይቃሉ ሆኖም ግን ችግሩ ከዞን አስተዳደሩ አቅም በላይ እንደሆነ ዝናሽ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል። 

የአለም አቀፍ ሰብአዊ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶችን  በተመለከተ፣ እኚህ ድርጅቶች ያለ በቂ አቅም እንደሚመጡ እናም ይሄ በቂ እንዳልሆነ ዝናሽ ትናግረዋል። “የዋግ ህዝብ ለሞት በረሃብ ምክንያት ተጋልጠዋል። ምክንያቱንም ባላውቅም ድርጅቶቹ በአከባቢው ነበሩ የተ.መ.ድ የሰብአዊ እርዳታ ማስተባበሪ ቢሮ ቢሆንም መጥቶ አይቷል ግን የልዩ አጋዥ መድሃኒቶች አላቀረቡም” መንግሥት ብቻ ነው እርዳታ እየሰጠ ያለው ብሏል።

የእብድ ውሻ በሽታ ወረርሽኝ ከዘጠኝ በላይ ልጆችን ህይወት የነጠቀ ሲሆን ይሄ አሀዝ  ከሞቱት መቶ ሀያ ሰዎች (በመድሃኒት እጥረት እና ረሃብ ምክንያት) በተጨማሪ ነው። ”

አበርገሌ ውስጥ ምንድንነው የተፈጠረው?

የወረዳው አስተዳዳሪ የሆኑት አለሙ ክፈሌ በአሁኑ ሰአት ከዋግ ኸምራ ወረዳዎች መሃል አንዱ የሆነው አበርገሌ ወረዳ በትግራይ ሀይሎች ቁጥጥር ስር ይገኛል ብለዋል። ከአበርገሌ ወረዳ የተሰደዱ 33,000 ሰዎች ሰቆጣ ውስጥ ይኖራሉ። እንደ አስተዳደሩ ገለጻ፣ አርሶ አደሮችን ወደ እርሻ እንዲመለሱ ብንጠይቅም እስከ አሁን  ማንም አልተመለሰም፣ ይሄ ደግሞ ለመጪ አመት የከፋ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል።

በተጨማሪም እንደ አለሙ አገላለጽ በዚህ ሰአት ነዋሪዎች እና ወረዳዎች (ያልተፈናቀሉት) ሁኔታ፣ “የእብድ ውሻ በሽታ ወረርሽኝ ከዘጠኝ በላይ ልጆችን ህይወት የነጠቀ ሲሆን ይሄ አሀዝ  ከሞቱት መቶ ሀያ ሰዎች (በመድሃኒት እጥረት እና ረሃብ ምክንያት) በተጨማሪ ነው። ” እንደ አስተዳዳሪ ከሆነ፣  ከእብድ ውሻ ወረረሽኙ በኋላ፣ ድንበር የለሽ ዶክተሮች በትግራይ ክልል በኩል ወደ ወረዳው ሁኔታውን ለመመርመር ገብቶ እንደ ነበር አስታውሰዋል። ከአዲስ ስታንዳርድ በነበራቸው ቃለ መጠየቅ የአለም ምግብ ድርጅት እርዳታ እየጠበቁ እንደሆነም ተናግረዋል።

በቅርቡ በወጣ ሪፖርት ፣ የወግ ኽምራ ዞን ከሃያ ሺ በላይ ከብቶች እንደሞቱ ተዘግቦ ነበር። ትናንት ግንቦት 9፣ 2014 ዓ.ም የጤና ቢሮው ባወጣው ደብዳቤ ለአማራ ክልል የህዝብ ጤና ተቋም ለህዝብ እርዳታ እና የጤና ምላሾች ለመስጠት እንደማይችል አሳዉቆ፣ ምክንያቱንም አከባቢዎቹ በትግራይ ሀይሎች ስር መሆናቸው ተንትኗል። በዛው ደብዳቤም የክልሉ ህዝብ ጤና ተቋም ከአለም አቀፍ እርዳታ ድርጅቶች ጋር ተባብሮ ለህዝቡ አፋጣኝ  ምላሽ እንዲሰጡ ተይቋል፣ አክለውም ስለ ወረረሽኙ ጥናት እንዲሰሩ፣እንዲቆጣጠሩት እና ተጓዳኝ የጤና አግልግሎትም እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

አዲስ ስታንዳርድ ከዚህ ቀደም ከዞኑ የተውጣጡ ተፈናቃዮች የተጠለሉበትን የመጠለያ ካምፕ አስመልክታ በካምፖች ውስጥ የንፅህና መጠበቂያ እቃዎች እጥረት እንዲሁም የመድኃኒት አቅርቦት ችግር መኖሩን ጠቅሳ የተለዩ የሽታዎች ወረርሽኝ ቢከሰት የዞኑ የጤና ቢሮው በቂ ዝግጅት እንደሌለው ዘግባ ነበር። ከችግሩም ጋር በተያያዘ ለምሳሌ ያህል ከአበርገሌ ወረዳ በተፈናቀሉ ሰዎች ላይ የእከክ በሽታ ታይቷል። በዚሁ ወረዳ በአሁኑ ጊዜ ከላይ የተጠቀሱት በሽታዎች በስፋት እየተስተዋሉ ይገኛሉ። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.