ዜና፡ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ፌደራል ፖሊስ ይግባኝ በመጠየቁ ከእስር አለመፈታቱ ተገለጸ

ቴዎድሮስ አስፋው- ፎቶ -ማህበራዊ ገፅ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13/ 2015 ዓ.ም፡– ኢትዮ ሰላም የተሰኘ የዩቱዩብ ቻናል መስራች ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ትንታኔ በመስጠት የሚታወቀው ቴዎድሮስ አስፋው በ30ሺ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ባሳለፍነው ሳምንት ፍርድ ቤቱ ብይን ቢሰጠም ፌደራል ፖሊስ ይግባኝ በመጠየቁ ከእስር አለመፈታቱን ጠበቃው አቶ ሰለሞን ገዛሀኝ እና ወንድሙ ቢንያም አስፋው ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።

ባሳለፍነው ሳምንት በ30ሺ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የግዜ ቀጠሮ ችሎት ብይን ሰጥቶ እንደነበር ጠበቃው አቶ ሰላሞን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ አርብ ዕለት የካቲት 10 ቀን 2015 ላይ የሚፈርም ሃላፊ የለም በሚል ሳይፈታ የሳምንቱን መጨረሻ ቀናት በእስር ቤት እንዲያሳልፍ መደረጉንም ወድንሙ አቶ ቢንያም ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል።

በዛሬው እለት የካቲት 13፣ 2015 ወደ ማረሚያ ቤት ያቀኑት ቤተሰቦቹ ፌደራል ፖሊስ ለፍርድ ቤት ይግባኝ በመጠየቁ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባል መባላቸውን ገልጿል።  

የካቲት 7 ቀን 2015 ስምንት ሰዓት አከባቢ ከመኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ኃይሎች ተወስዶ መታሰሩን ወንድሙ ቢንያም አስፋው በቻናሉ ቀርቦ በሰጠው ቃለምልልስ ማስታወቁን አዲስ ስታናዳርድ መዘገቧ  ይታወሳል። ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው በወቅታዊ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የከረረ ትችት በመንግስት ላይ በማቅረብ ይታወቃል። ቴዎድሮስ ለመጨረሻ ግዜ በዩቱዩብ ቻናሉ የቀረበው የካቲት 2 ቀን 2015 ‘’ከሲኖዶሱ ህልውና ጋር የተያያዘው ሰላማዊ ሰልፍ’’ በሚል ርዕስ እንደነበር ከቻናሉ ለማወቅ ተችሏል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.