ዜና፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ100,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲወጣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

በማህሌት ፋሲል

አዲስ አበባ ሰኔ 27 ቀን፣ 2014 ዓ.ም፣ ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስት ጉዳዩች እና የፀረ ሽብር ችሎት የቀረበው የፍትሕ መጽሔት ባለቤት እና ማኔጂንግ ዳሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በተከሰሰበት ሶስት የወንጀል ክሶች የ 100,000 ሺ ከእስር እንዲወጣ ተፈቀደለት።

በዛሬው እለት ከሰአት በኋላ በዋስትና ላይ ብይን የሰጠ ሲሆን በሁለት ዳኞች የዋስትና ፍቃድ እና በአንድ ዳኛ ተቃውሞ ባብላጫ ድምጽ ዋስትና ው ተፈቅዷል። በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የቀረበው ክስ መቃወሚያ ጠበቆች በጹሁፍ ለሃምሌ 11 2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ሰኔ 22 ቀን በዋለው ችሎት ጠቅላይ አቃቤ ህግጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ 1ኛ ክስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 44(1)፣ (2) እና 336(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ የአገር መከላከያ ሚስጥርን በማውጣት ሲሆን 2ኛ ክስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 44(1)፣ (2) እና 337(1) ስር የተመለከተውን በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የሚያደናግር ወይም የሀሰት መረጃ በመተላለፍ እና 3ኛ ክስ በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 44(1)፣ (2) እና 257(ሠ) ስር የተመለከተውን ወንጀል በማነሳሳት እና በመገፋፋት የሚል 3 ተደራራቢ ክስ ማቅረብ የሚታውስ ነው። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.