ዜና፡ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ተወያዩ፤ ሩሲያ ለአፍሪካ አገራት ነፃ የእህል ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20/2015 ዓ.ም፡- የሩሲያ- አፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ ወደ ሩሲያ ያቀኑት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በትላንትናው እለት ከሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን ጋር በቅዱስ ፒተርበርግ መምከራቸውን አለም አቅፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ እና ታሪካዊ ግንኙነት አጠናክረው በቴክኖሎጂ፣ በሳይበርሴኩሪቲ፣ በኢኮኖሚ እና በንግድ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመሥራት መነጋገራቸው ተገልጧል።

ፑቲን “በዚህ ጉባኤ በዓለም መድረክ ላይ አቋሟን ይበልጥ በማንጸባረቅ ላይ ከምትገኘው የአፍሪካ አህጉር ጋራ ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የሚረዳ ከፍተኛ ኹነት ነው” ሲሉ የገለፁ ሲሆን ሁለቱ አገራት በወቅታዊ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ አንድ አይነት አቋም አላቸው ሲሉ ብለዋል፡፡

ፑቲን ሪሲያ በቅርቡ ከጥቁር ባሕር የእህል ስምምነት መውጣቷን በተመለከተ በሰጡት አስተያየት፣ ሩሲያ ለየአፍሪካ አገራት ነፃ የእህል ድጋፍ እንደምታደርግ ደጋግመው አረጋግጠዋል ሲል ኤፒ ዘግቧል፡፡

“ዩክሬን ለአፍሪካ የምታደርገውን የእህል ድጋፍ ሪሲያ በንግድና ከክፍያ ነፃ በሆነ መልኩ እደምትተካው ለረጋግጥላችሁ ፈልጋለሁ” በማለት የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፣ ሩሲያ በስድስት ወራት ውስጥ 10 ሚሊዮን ቶን እህል ወደ አፍሪካ ማጓጓዟን  ሰኞ እለት በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸው በዘገባው ተመላክቷል፡፡

በዛሬ እለት 2ኛው የሩሲያ- አፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ የሚከናወን ሲሆን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መሪዎቹ ይመክራሉ፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.