ዜና፡ እኛለኛ በስደት የተባለ ግብረ-ሰናይ ተቋም ከስደት ተመልሰው የስራ አማራጮች ላጡ ዜጎች ነፃ የሙያ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መክፈቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሓምሌ 20 / 2015 ዓ.ም፡- በስደተኞች ጉዳይ ላይ በመስራት የሚታወቀው “እኛለኛ በስደት” የተባለ ግብረ-ሰናይ ድርጅት፣ ከብዙ እንግልት በኋላ ከስደት ተመልሰው የስራ አማራጮች ላጡ  እህቶች  ነፃ የሙያ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ከፍቶ በማሰልጠን ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ማሰልጠኛውን ለመክፈት የተፈለገው ከስደት ተመላሾች የስራ አማራጮች በማጣታቸው ለተጨማሪ ጭንቀት በመዳረጋቸውና  አዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ የግል ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶች ላይ አስመዝግቦ የማስተማር አካሄድ ዘላቂነት በማጣቱ ምክንያት መሆንን ተቋሙ ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው መግለጫ ተልጧል፡፡

በመሆኑም ተቋሙ ጠቅላላ ከሊባኖስ ከሳዑዲ አረቢያ ከኤሚሬት ከኦማንና ከየመን ከብዙ ስቃይ በኋላ ወደ ሀገራቸው ለተመለሱ ሴቶች በታህሳስ 2015 ዓ.ም  “እኛለኛ ከስደት ተመላሾች የሙያ ትምህርት ቤት” በሚል ማሰልጠኛ ከፍቶ ተመዝጋቢዎችን ያለ ክፍያ በጸጉር ስራና በልብስ ዲዛይን በማስተማር ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ለሰው ቤት ሰራተኞች ብቻ በተከፈተው ይህ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት 200 ተማሪዎች በተለያዩ ፈረቃዎች አስመዝግቦ በዚህ ሰዓት ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ ያለው ግርጅቱ በከፊል እንድ ድርጅቱ አቅም የተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪን እንደሚሸፍን አክሎ አስታውቋለል።

በማሰልጠኛ ተቋማት የመመዝገብያ ቦታ ውስን በመሆኑ ይሄንን አገልግሎት በቁጥር አነስ ላሉ ተመላሾች ብቻ እንድናበረክት ምክንያት ሆኗል ያለው እኛለኛ በስደት፣ በኢትዮጵያ ያሉ የባለ ድርሻ አካላት ለነዚህ እህቶች በአገራቸው ሰርተው እንዲለወጡ መፍትሄ እንዲያበጁ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ይህ ግብረ ሰናይ ድርጅት በሊባኖስ በስደት ላይ ካሉት የቤት ሰራተኞች መካከል 68 ከመቶ ለጾታዊ ትንኮሳ መዳረጋቸውን ሊባኖስ ከሚገኘው የሊባኖስ አሜሪካን ዪኒቨርሲቲ ጋር በመሆን ባዘጋጀዉ ጥናት ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡

የእኛለኛ በስደት ተቋም ሊባኖስ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሰው ቤት ሰራተኞች በ2009 ዓም የተቋቋመና በስደት ላይ ላሉት የሰው ቤት ሰራተኞች ጥብቅና የሚቆም በጎ አድራጎት ድርጅት ነው። ድርጅቱ ሊባኖስ ላሉትና በብዙ እንግልት የሚያልፉ ለሰው ቤት ሰራተኞችን የሰብዓዊ እርዳታ በማበርከት እስር ቤት ለታሰሩት ጠበቃ በመቅጠር እና ወደ ኢትዮጵያ የመመለሻ ትኬት እና ሌሎች ወጪዎች በመሸፈን ላለፉት ስድስት ዓመታት ስደተኛ እህቶችን ሲያገለግል ቆይቷል። 

የእኛለኛ በስደት ተቋም ከ2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ምዝገባው ተጠናቅቆ ቢሮ ከፍቶ ከመካከለኛው ምስራቅ ለተመለሱት እህቶች የተለያየ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በመስራት ላይ ይገኛል። ተቋሙ ባለፉት 3 ዓመታት በሊባኖስ አስከፊ ችግር ላይ ወድቀው የነበሩ ከ800 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ሙሉ ወጪያቸው ሸፍኖ ነበር። በሊባኖስ በአሰሪዎቻቸው ጥቆማ ክስ የቀረበባቸውና ታስረው እስር ቤት የገቡ ከ200 በላይ ኢትዮጵያውያን ሴቶች የህግ ውክልና መድበንላቸው በጠበቃችን እገዛ ከ3 እህቶች ውጪ በሙሉ ክሳቸው ተነስተው ወደ ሃገራቸው መመለስ ችለዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.