በማህሌት ፋሲል
አዲስ አበባ የካቲት 21 2014፣ የካቲት 17፣ 2014 በዋለው ችሎት ፖሊስ በጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ላይ ምርመራውን ለማጠናቀቅ በጠየቀው መሰረት የገላን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀን ፈቀደ።
ከዚህ ቀደም ፖሊስ በ‹ተራራ ሚዲያ ግሩፕ› የዩቲዩብ ቻናል ላይ ስርጭት ፈጽሟል ያላቸውን ስምንት ጥሰቶች በመጥቀስ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ጠይቋል።
አዲስ ስታንዳርድ ከፍርድ ቤት የደረሳትን ሰነድ ያየች ሲሆን በክሱም ውስጥ “ የሃገሪቱ አንድ ክፍል የሆነውን የኦሮሞ አንድነት እንዲበታተን የሚያነሳሳ” የሚል እና “የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚደንት ሽመልስን በስም በመጥራት፣ የተሳሳተ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግርን በክልሉ አመራሮች ላይ በማሰራጨት” የሚል ይገኘበታል።
ሰነዱ ላይ ታምራትን “አንድ አመት በቆየው ጦርነት ለህወሃት የሚጠቅም መረጃ በማራገብ” እና “ስለ ጦርነቱ ሂደት ሆን ብሎ የተሳሳተ መረጃ በሚድያ በማሰራጨት” በሚል ክስ ቀርቦበታል።
ተጨማሪም ፖሊስ ህወሃት እና ኦነግ ካደረሱት የጦርነት ውድመት ባልተናነሰ መልኩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሆን ብሎ የሃገሪቱን ስም በሚያጎድፍ እና ዝቅ በሚያደርግ መልኩ እየሰራ ነው” ብሏል በሚል ክስ ቀርቦበታል። ፖሊስ አያይዞም ጥቅምት 23፣ 2014 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመተላለፍ ህወሃትን በማበረታታት እና ህዝብን የመረበሽ አላማው እንዲሳካ መረጃ በመስጠት በሚል ክስ አቅርቧል።
ሌላው ታምራት የተከሰሰበት ደግሞ በብሄር ብሄረሰቦች ላይ የጥላቻ ንግግርን በማሰራጨት የሚል ነው። እንደ ፖሊስ ክስ ታምራት ብሄር ብሄረሰቦችን “ገተት” ብሎ ጠርቷል የሚል ሲሆን ይህ እና መሰል ጥሰቶች የህገ-መንግስ መናድ፣ ብጥብጥ እና ሽብርተኝነት ሊፈጥር ይችላል ብሏል።
የጋዜጠኛው ጠበቃ አቶ ገመቹ ጉልማ ለአዲስ ስታንዳር እንደተናገሩት ፖሊስ ምርመራውን ለፍርድ ቤት አሳውቋል። አክለውም “ከደንበኛዬ እጅ ተገኙ ያላቸውን 32 የሚደርሱ የኤለክትሮኒክስ መሳሪያዎች የምርመራ ውጤት ስላልደረሰ 14 የምርመራ ቀን ይፈቀድልኝ ብሎ በመጠየቁ ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ተቀብሎታል” ብለዋል።
እኛም ተጨማሪ የምርመራ ቀን መሰጠት የለበትም ብለን የተለያዩ ነጥቦችን አንስተን ተከራክረናል ያሉት አቶ ገመቹ “የኦሮሚያ ፖሊስ የምርመራ ቀን እየጠየቀ ያለው ተፈፀመ የሚላቸው ወንጀሎች በሚዲያ የተፈፀሙ ናቸው። የኢትዩጵያ መገናኛ ብዙሀን አዋጅ በሚዲያ ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን በተመለከተ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ተጠርጣሪው በእስር ለምርመራ ከቀረበ በኋላ አቃቤ ህግ ክስ ይመሰርታል ነው የሚለው። ስለዚህ የግዜ ቀጠሮው መፈቀድ የለበትም ብለን ተከራክረናል” ብለዋል።
ፖሊስም ከሚዲያ ስራ ውጪ የሆነ ወንጀል እየመረመርኩ ነው ሲል ለችሎቱ ተናግሯል ያሉት አቶ ገመቹ ባለፈው የግዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ላይ የሌለ አሁን ላይ ግን ከኦነግ ሸኔ እና ከህውሀት ጋር እየተገናኘ የሽብር ተግባር ፈፅሟል ሲል የኦሮሚያ ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል ብለዋል። አቶ ገመቹ ፖሊስ ላቀረበው የሽብር ወንጀል መመርመርም ሆነ መዳኘት ያለበት በፌደራል ፖሊስ እና በፌደራል ፍርድ ቤት ነው ስለዚህ ይህ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ለመስጠት ስልጣን የለውም ብለን ተከራክረናን በማለት ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል። አቶ ገመቹ አክለውም ደንበኛቸው በእስር በቆየበት ሁለት ወር ከ17 ቀን ክስ ከመመስረትም ባሻገር ፍርድ ለማግኘት በቂ ጊዜ ስለሆነ በዋስ ተለቆ ክሱን ይከታተል ሲሉ እንደተከራከሩ አስረድተዋል። ፍርድ ቤቱ የኛን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ቀን ሰጥቶ ተለዋጭ ቀጠሮ ለመጋቢት 1 2014 ዓም ተወስኗል።
ታህሳስ 21፣ 2014 በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ገላን ወረዳ ፍርድ ቤት የታምራት ነገራን ጉዳይ ወደ አስቸኳይ ኮማንድ ፖስት ማስተላለፉ ይታወሳል። በወቅቱም ፖሊስ የጋዜጠኛውን የክስ መዝገብ እንደዘጋ እና ተጨማሪ ምርመራ የተራራ ኔት ወርክ ዋና አዘጋጅ ታምራት ነገራ ታህሳስ 1፣ 2014 ከሚኖርበት ቤት የተወሰድ ሲሆን “ከጠዋቱ 4:30 ለጥያቄ ትፈለጋለህ” ተብሎ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንደተወሰደ ባለቤቱ ሰላም ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግራ ነበር። ባላቤቱ አክላ እንደገለጸችው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ አዲስ አበባ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የተወሰደ ሲሆን በወቅቱም ፖሊስ ምንም አይነት ማብራሪያ እንዳልሰጠ ተናግራለች። እንደማያስፈልገው ያስታወቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ወደ ኮማንድ ፖስት እንዲመራው ጠይቆ ነበር። አስ